የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

ምክር ቤቱ ሦስት አዋጆችን አፀደቀ

Jul 1, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 23/2018 (ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስና የኢትዮጵያ ካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጆችን አፀደቀ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 29ኛ መደበኛ ስብሰባ ከአዋጅ ማፅደቅ በተጨማሪ የፌዴራል መንግስት የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት እቅድ ላይ በዝርዝር ተወያይቷል።


የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጄ ረቂቅ አዋጆቹን የተመለከተ ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ሰብሳቢው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ በታክስ ከፋዩና በታክስ ሰብሳቢው የሚነሱ አለመግባባቶችን ለመፍታት፣ ተጠያቂነትና ፍትሐዊነትን ለማስፈን ብሎም ዘመናዊ የታክስ አስተዳደር ስርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

አዋጁ ገለልተኛ አስማሚ እንዲመደብ በማድረግ አለመግባባቶችን በአማራጭ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል በመሆኑ ምክር ቤቱ እንዲያፀድቀው ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ረቂቅ አዋጅ የዕድገት ጉዞና የለውጥ ፕሮግራሞች እንዲሁም የፖሊስ አወጣጡን በመረጃ ላይ የተደገፈ ለማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል።

ዘመናዊ ጠንካራና ህጋዊ መሰረት ያለውና ዓለም አቀፍ ስርዓትን የተከተለ የስታቲስቲክስ ማዕቀፍ እንዲኖር የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።


የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጄ የኢትዮጵያ ካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጅ እያደገ የመጣውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ወደ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማሻገር፣ የአረንጓዴ ኢንቨስትመንትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማሳለጥ የሚረዳ ነው ብለዋል።

ምክር ቤቱ በቋሚ ኮሚቴው የቀረቡ የውሳኔ ሃሳቦችን በመመርመር ሦስቱን ረቂቅ አዋጆች አጽድቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026