የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የኢትዮጵያ ከተሞችን የማዘመንና የማልማት ተግባራት አዳዲስ አሰራሮችን መተግበር ይፈልጋል

Sep 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ከተሞች ዘመናዊነትን አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ የአሰራር ሥርዓቶችን ማዘመን፣ የዲጂታልና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ እና ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ልማትን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በኢንዱስትሪ፣ ከተማና መሰረተ ልማት የጥናትና ምርምር ማዕከል የተጠናውን "በኢትዮጵያ የስማርት ከተማ ልማት አሠራሮች፡ ከስማርት አስተዳደር፣ ከትራንስፖርት እንቅስቃሴ እና ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር" በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን ሀገራዊ የጥናት የመፍትሔ ምክረ-ሐሳብ ይፋ አድርጓል፡፡


የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል አሕመድ ሃምዛ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ሀገሪቱ የያዘችውን የብልፅግና ጉዞ ለማሳካት እንዲሁም በ2030 በቴክኖሎጂ የታገዘ ኢንደስትሪላይዜሽን የመገንባት እቅድን በጥናትና ምርምር ለመደገፍ እየተሰራ ይገኛል።

በዚሁ መሠረት ተቋሙ በአማካይ በየዓመቱ ከ50 በላይ የጥናትና ምርምር ስራዎችን እንደሚያከናውን ጠቅሰው፤ የአሁኑ ጥናትም ከተሞችን ዘመናዊና ስልጡን ለማድረግ የሚያስችሉ የፖሊሲ ስትራቴጂ አቅጣጫዎችን አመላክቷል ብለዋል።

የስማርት ከተሞች ግንባታን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ የተቋማት የተቀናጀ አሰራርንና ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ የትራንስፖርት አገልግሎትን ማስፋፋት፣ ወጥ የሆነ የስማርት ከተማ አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የተደራጀ የመረጃ አያያዝና ሳቢ ህጎችን መቅረጽ፣ የሰው ኃይል፣ የፋይናንስና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ስርዓትን ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም አሁን ላይ እንደ ሀገር የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ይህም ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡


በኢንስቲትዩቱ የከተማና መሠረተ ልማት ዘርፍ ተመራማሪ አቶ ተካልኝ አርፍጮ በበኩላቸው፤ ጥናቱ በኢትዮጵያ በኮሪደር ልማት የተመዘገቡ ስኬቶችን በዘላቂነት ማስቀጠል ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮሪደር ልማት የመንገዶችን ሁኔታ በማሻሻልና ለነዋሪዎች እንቅስቃሴ ምቹነትን በመፍጠር ረገድ ተጨባጭ ውጤት ማሳየቱን በመጥቀስ፣ እነዚህ መሰረተ ልማቶች ለስማርት ሲቲ ግንባታ ትልቅ አቅም በመሆናቸው ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የስልጡን ከተሞች ግንባታ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑን አመልክተው፤ ከመንግስት በተጨማሪ የግሉ ዘርፍ ባለሀብቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ሊጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራ አማራጮችን ወደ ውጤት የመቀየር ተግባራት ይጠናከራሉ

ሆሳዕና ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ) ፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራ አማራጮችን ወደ ውጤት የመቀየር ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክል...

Sep 20, 2026

የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማረጋገጥ ብሔራዊ ጥቅም የማስጠበቅና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ጉዳይ ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማስመለስ ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥና ቀ...

Sep 18, 2026

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026