የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በዞኑ በመኸር ወቅቱ በመካናይዜሽን ለታገዘ ኩታ ገጠም እርሻ ትኩረት ተሰጥቷል

May 20, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዳማ፣ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በመኸር ወቅቱ የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ በመካናይዜሽን ለታገዘ ኩታ ገጠም እርሻ ትኩረት መሰጠቱ ተገለጸ።

በዞኑ ለምርት ወቅቱ የሚያስፈልግ የምርት ማሳደጊያ ግብአትም በወቅቱ እየተሰራጨ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል።

የእርሻ መካናይዜሽን የጉልበት ሥራን በሚተኩ እንደ ትራክተርና ኮምባይነር ባሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችና ማሽኖች ግብርናን ማዘመን ሲሆን አሰራሩም ጊዜን፣ ጉልበትና ወጪን በመቀነስ የምርት መጠንንና ጥራትን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ነው።

በዚህም መንግስት በሀገሪቱ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመንና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የመካናይዜሽን እርሻን በስፋት ለመጠቀም ግብ ጥሎ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

ከዚሁ ጋር በተገናኘ ኢዜአ በምስራቅ ሸዋ ዞን የ2018/19 ምርት ዘመን የመኸር ወቅት እርሻ ገጽታ በተመለከተ ከዞኑ ግብርና ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አብነት ዘገየ ጋር ቆይታ አድርጓል ።

አቶ አብነት እንደገለጹት በዞኑ በመኸር ወቅቱ 512 ሺህ 622 ሄክታር መሬት ላይ የተለያዩ ሰብሎችን በማልማት ከ20 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።

በምርት ወቅቱ የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ በመካናይዜሽን ለታገዘ ኩታ ገጠም እርሻ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል።

በዚህም በምርት ወቅቱ አጠቃላይ ከሚለማው መሬት ውስጥ ከ410 ሺህ ሄክታር በላይ በኩታ ገጠም እንደሚለማ ገልፀው እስካሁን ድረስ ከ200 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነው በትራክተር በመታገዝ መታረሱን ተናግረዋል።

በዞኑ ከሚያዚያ 2018 ዓ.ም መጨረሻ አንስቶ የአገዳ ሰብሎችን መዝራት እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው በሰኔ 2018 ዓ.ም ደግሞ የብርእ ሰብሎች በስፋት እንደሚዘሩ አመልክተዋል።

በመኸር ወቅት እርሻው ከ195 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እየተሳተፉ መሆናቸውን ጠቅሰው በምርት ወቅቱ የተያዘውን ግብ ለማሳካት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና የግብርና ባለሙያዎች ለአርሶ አደሩ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን አውስተዋል።

የምስራቅ ሸዋ ዞን ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አስራት ጌቱ በበኩላቸው በምርት ዘመኑ ለዞኑ ከሚያስፈልገው አንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ዳፕና ዩሪያ ማዳበሪያ ውስጥ ከ900 ሺህ ኩንታል በላይ የሚሆነው መቅረቡን ተናግረዋል።


እስካሁን ድረስ 537 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በህብረት ስራ ማህበራት በኩል ለአርሶ አደሮች መሰራጨቱን ጠቁመው አርሶ አደሮችም ማዳበሪያን በመጠቀም የግብርና ስራቸውን እያሳለጡ ይገኛሉ ብለዋል።

በተጨማሪም ጤፍና ስንዴን ጨምሮ ከ68 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ባለፉት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ባለፉት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁ...

May 15, 2026

ረቂቅ አዋጁ የወጪና የገቢ ንግድን ለማሳለጥ የጎላ አስተዋፅኦ ይኖረዋል

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡-የጉምሩክ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ የወጪና የገቢ ንግድን ለማሳለጥ የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው በህዝብ ተወካዮች ምክር ...

Apr 23, 2026

ኢትዮጵያ እና አይኤምኤፍ በኢኮኖሚው መስክ ትብብራቸውን ያጠናክራሉ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጎ...

Apr 17, 2026

በጀጎል ግንብ ውስጥ የሚገነባው የ”ዳር ሀረር” የመልሶ ማልማት ፕሮጀክት ግንባታ ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦ የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ ውስጥ የሚገነባው የ''ዳር ሀረር'' መልሶ ማልማት ፕሮ...

Apr 12, 2026