የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በኦሮሚያ ክልል ለመኸር እርሻው እስካሁን ከ4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ተሰራጭቷል

Jun 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ለመኸር እርሻው እስካሁን ከ4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ እንዳሻው ጀማነህ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በክልሉ በመኸር እርሻ 11 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሄክታር መሬትን በማልማት ከ380 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዷል።

አጠቃላይ በመኸር እርሻ ከሚለማው መሬት ውስጥም 8 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሄክታሩ በኩታ ገጠም የእርሻ ስነ-ዘዴ የሚለማ መሆኑን ጠቁመዋል።

በክልሉ እስካሁን ባለው ሂደት ከ8 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት መታረሱን ጠቅሰው፣ ከዚህ ውስጥ ከ2 ሚሊዮን 823 ሺህ በላይ ሄክታሩ በተለያዩ የሰብል ዓይነቶች መሸፈኑን ተናግረዋል።

በምርት ዘመኑ የታቀደውን ግብ ለማሳካት የግብዓት አቅርቦቱ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ለመኸር እርሻው ከ14 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለማቅረብ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ጠቅሰው፣ እስካሁን ከ8 ሚሊዮን 454 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ በሕብረት ሥራ ማህበራትና በዩኒየኖች በኩል እየተሰራጨ መሆኑን ተናግረዋል።

ለማህበራቱና ለዩኒየኖቹ ከደረሰው ማዳበሪያም ከ4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሚሆነው ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን ገልጸዋል።

ከታቀደው 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ውስጥ 378 ሺህ 426 ኩንታሉ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የደረሰ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 355 ሺህ 73 ኩንታሉ ለአርሶ አደሩ በወቅቱ ተከፋፍሏል ብለዋል።

በክልሉ በአሁኑ ወቅት ያለው የዝናብ ሁኔታ መልካም በመሆኑ፣ አርሶ አደሩ ይህንን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በእርሻ ሥራው ላይ በንቃት እየተሳተፈ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

ለመኸር እርሻው ስኬታማነት ከክልል እስከ ታችኛው መዋቅር የሚገኙ አመራሮችና የግብርና ባለሙያዎች ለአርሶ አደሩ የቅርብ ክትትልና ጠንካራ ሙያዊ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑንም አቶ እንዳሻው ጨምረው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026