🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 2/ 2018(ኢዜአ):- የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር (EAPP) 22ኛው የሚኒስትሮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) እና የአባል ሀገራቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ የወቅቱ የትስስሩ ሊቀመንበር (ሰብሳቢ) ስትሆን፤ ዛሬና ነገ በአዲስ አበባ በሚካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ በልዩ ልዩ አጀንዳዎችና ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ትስስሩ 13 ሀገራትን በአባልነት ያቀፈ ሲሆን፤ በአባል ሀገራቱ መካከል የኤሌክትሪክ ኃይልን በጋራ ለመጠቀም፣ የኃይል ግብይት ለማካሄድ እና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል ታልሞ የተመሠረተ ነው።
ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ታንዛንያ፣ ኡጋንዳ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ግብፅ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ሊቢያ የጥምረቱ አባል ሀገራት ናቸው።
የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር እ.አ.አ በየካቲት ወር 2005 የተመሠረተ ሲሆን፤ ዋና መሥሪያ ቤቱም በአዲስ አበባ ይገኛል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026