የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የጉምሩክ ኮሚሽን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ738 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

Jul 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 2/ 2018(ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 738 ነጥብ 14 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) ገለፁ።

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) የተጠናቀቀውን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ክንውን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።


የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ፤ በበጀት ዓመቱ 725 ነጥብ 27 ቢሊዮን ብር ለማግኘት አቅዶ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል።

በዚህም በተከናወኑ ውጤታማ ሥራዎች 738 ነጥብ 14 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታውቀዋል።

የተገኘው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ77 ነጥብ 56 በመቶ ብልጫ ያስመዘገበ እንደሆነ አመላክተዋል።

ኮሚሽኑ ሀገሪቱ ከቀረጥና ታክስ ተገቢውን ገቢ እንድታገኝ በማድረግ፣ የኮንትሮባንድና ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን በመከላከልና በመቆጣጠር እንዲሁም የወጪ ንግድ እንዲሳለጥ የሚጠበቅበትን ሚና መወጣቱንም ጠቁመዋል።

የተሰበሰበው ገቢ ከወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ፣ በወጪ ንግድ ላይ ከሚስተዋል የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ እንዲሁም ከሌሎች ኮሚሽኑ ካከናወናቸው ተግባራት የተገኘ መሆኑን አብራርተዋል።

የመንግሥት የፖሊሲ አቅጣጫዎች ለዘርፉ የተመቹ መሆን፣ የተደረጉ ተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች እና አሠራርን በቴክኖሎጂ የማዘመን ተግባራት ለገቢው ማደግ አቅም መፍጠራቸውን ገልጸዋል።

የጉምሩክ ኮሚሽን በ2019 የበጀት ዓመት ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱንም አስታውቀዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሕገወጥ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን የመቆጣጠር ሥራን በማጠናከር፥ ከዘርፉ ጥቅም ማስገኘት ያስቻሉ ውጤታማ ሥራዎች መሰራታቸውን አስገንዝበዋል።

በገቢና በወጪ እቃዎች ላይ በተሰራው የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን የመከላከል ሥራም 28 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር የሚገመቱ ምርቶች መያዛቸውንም አብራርተዋል።

በኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ላይ በተደረገ ቁጥጥር ከተያዙ ምርቶች መካከል ኤሌክትሮኒክስ፣ መድሃኒት፣ አደንዛዥ እጽ፣ የቁም እንስሳት እና ሌሎች እንደሚገኙበት አመላክተዋል።

አሁንም በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እያሳደረ ያለውን የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026