የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በሐረሪ ክልል 47 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ ገብተዋል

Aug 7, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል በ2018 በጀት ዓመት 47 አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ መግባታቸውን የክልሉ ኢንተርፕራይዝ ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ ወደ ስራ የገቡ ኢንዱስትሪዎች ለዜጎች የስራ እድል እየፈጠሩ መሆናቸውም ተገልጿል።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ ሃምዲ ሰለሃዲን እንደገለጹት በክልሉ በተለይም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪውን የማምረት አቅም ከማጎልበት ባለፈ በዘርፉ መነቃቃት እንዲፈጥር እያስቻለ ነው።

ወደ ስራ የገቡት ኢንዱስትሪዎች ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶችን በማጎልበትና ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጪ ምንዛሬን እያስቀሩና ለኢኮኖሚው ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከቱ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 47 መካከለኛ እናአነስተኛ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ እንደገቡ ገልጸው፣ ተጨማሪ 16 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ደግሞ የግንባታ ሥራቸውን አጠናቀው ወደ ማሽነሪ ተከላ ሥራ መግባታቸውን ተናግረዋል።

ሥራ የጀመሩ ኢንዱስትሪዎችም ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጪ ምንዛሬን ከማስቀረት አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከቱ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

አምራች ኢንዱስትሪዎቹ ከሃይል አቅርቦትና ከመሰረተ ልማት ጋር በተያያዘ ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት መሰራቱን ገልጸው ዘንድሮ በኢንዱስትሪ ዘርፉ ብቻ3 ሺህ 935 ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ እድል ተፈጥሯል ብለዋል።

በቀጣይም የኢንዱስትሪ ዘርፍ የማጎልበት ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉም አቶ ሀምዲ ገልጸዋል።

በፋብሪካዎቹ የስራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶችም እራሳችውንና ቤተሰባቸውን ከመደጎም ባለፈ ልምድ እየቀሰሙና በትርፍ ጊዜያቸውም የኮሌጅ ትምህርት እንዲከታተሉ እድል እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

በሐረሪ ክልል 196 ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ አምራች ኢንዳስትሪዎች በማምረት ስራ ላይ እንደሚገኙም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የ25 ዓመት የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ እና ማሻሻያ ማስተር ፕላን ጥናት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እስከ ፈረንጆቹ 2049 ድረስ የሚተገበር የ25 ዓመታት ሀገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ማስ...

Jul 28, 2026

የኢትዮጵያ የመንገድ መሰረተ ልማቶች የሕዝብን የኢኮኖሚ ትስስር በማሳለጥ የብልፅግና ድልድይ እየገነቡ ነው

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 16/2018 (ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያ መንገድ መሰረተ ልማቶች የሕዝብን የኢኮኖሚ ትስስር በማሳለጥ የብልፅግና ድልድይ እየገነቡ መሆኑን የከተማ...

Jul 24, 2026

በጅማ ዞን የሩዝ ምርታማነት እያደገ መጥቷል

ጅማ፤ ሐምሌ 14/2018(ኢዜአ)፦ በጅማ ዞን የሩዝ ሰብልን ለማስፋፋት በተከናወነው ሥራ ምርታማነቱ እያደገ መምጣቱን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ገልጿል። በዞኑ...

Jul 22, 2026

በሰሜን ሸዋ ዞን ከ199 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የጠጠር መንገዶች ተገንብተዋል

ደብረ ብርሃን ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በ199 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ 72 ኪሎ ሜትር የጠ...

Jul 18, 2026