አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 24/20017(ኢዜአ)፦ ኢቢሲ አሁን ካለው ደረጃ ወደ ተሻለ ምእራፍ እንዲሸጋገር መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ሸጎሌ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና መሥሪያ ቤት ጎብኝተናል ብለዋል፡፡
ኢቢሲ የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህልና ማህበራዊ እሴቶች በማስተዋወቅ እና ለመልካም ገፅታ ግንባታ እያደረገ ያለው ጥረት ለሌሎች መገናኛ ብዙኃን ምሳሌ መሆን የሚችል ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ተቋሙ ዘመኑን የዋጀ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ከመገንባት ባሻገር "ወደ ይዘት" በሚል መሪ ቃል በጀመረው የይዘትና የአቀራረብ ማሻሻያ ተደራሽነቱን ለማስፋት እየሠራቸው የሚገኙ ተግባራት አበረታች ናቸው ነው ያሉት፡፡
ኢቢሲ በተለያዩ ክልሎች አዳዲስ ስቱዲዮዎችን ገንብቶ ወደ ሥራ ማስገባቱ የኢትዮጵያን አዎንታዊ መልክ ለማጉላትና የወል ትርክትን ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
ተቋሙ ተአማኒና ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ለመሆን፣ የሀገርን ታሪክና ባህል ለማስከበር እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲፈጠር፤ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡
ኢቢሲ አሁን ካለው ደረጃ ወደ ተሻለ ምእራፍ እንዲሸጋገር መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025