ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲ እና የጋምቤላ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር)፣ በብልፅግና ፓርቲ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍቅሬ አማን እንዲሁም ሌሎች የክልልና የዞን አመራሮች ተገኝተዋል።
ከፍተኛ አመራሮቹ በቦንጋ ከተማ በማህበራትና በግለሰቦች የሚከናወኑ የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር ሰራዎችን ነው እየጎበኙ የሚገኙት።
አመራሮቹ በጉብኝታቸው በእንሰሳት እርባታ ዘርፍ የተሰማራ ድርጅትን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።
የድርጅቱ ባለቤት አቶ ዮናስ ገዛሃኝ፤ ስራ ከጀመሩ አስራ አንድ አመታትን ማስቆጠራቸውን ገልጸው በዚህ ወቅትም የተሻለ ደረጃ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ድርጅቱ የወተት ምርቱን ለማሻሻል የመኖ ልማትና ማቀነባበር እንዲሁም ዝርያ ማሻሻል ላይ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
በቀን እስከ 550 ሊትር ወተት እንደሚያመርትና ምርቱን በስፋት ለገበያ እያቀረበ መሆኑን አመልክተዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025