አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ መልኩ ስራ ላይ እንደሚውል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የዲጂታል ግብይት ስርዓቱን አስተማማኝ ለማድረግ እየተከናወነ ያለው የሳይበር ደሕንነት ስራ ውጤታማ መሆኑም ተገልጿል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሹሩን አለማየሁ(ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት በቀጣይ አመት ሁለተኛው ዙር የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 መርሐ ግብር ይጀመራል።
መርሐ ግብሩ ትኩረት ከሚሰጣቸው ተግባራት መካከል በወረቀት ገንዘብ የሚካሔድ ግብይትን ማስቀረትና በወረቀት የሚካሔዱ አገልግሎቶችን የሚያስቀሩ እንደሆነም ነው የገለጹት።
በኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስርዓት በስፋት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው፤ አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ምቹ የግብይት ስርዓት ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ከዚህ ውስጥም በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የግብይት ስርዓቱን በማዘመን በወረቀት ገንዘብ የሚካሔድ ግብይትን ማስቀረትና ከወረቀት ንክኪ የፀዳ አገልግሎት ተግባራዊ ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለፃ በመጀመሪያው ዙር የዲጂታል ኢትዮጵያ መርሐ ግብር የመንግስት አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ነው የገለጹት።
በአሁኑ ወቅትም በ25 የመንግስት ተቋማት 800 በላይ አገልግሎቶች ዲጂታል ቴክኖሎጂን ተጠቅመው እየሰሩ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ባለፉት ጥቂት አመታት ቴሌብርና የንግድ ባንክ የዲጂታል አመራጮችን ጨምሮ በሌሎች የዲጂታል ዘርፎች በተካሔደው ግብይት በትሪሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ማዘዋወር ተችሏል ነው ያሉት።
በመሆኑም የግብይት ስርዓቱን አስተማማኝ ለማድረግ እየተከናወነ ያለው የሳይበር ደህንነት ስራ ውጤታማ በመሆኑ እቅዱን ለማሳካት ምቹ መደላድል መፈጠሩን ጠቅሰዋል።
እስካሁን ባለው ሒደት ከ11 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ የወሰዱ መሆናቸውንም ነው ሚኒስትር ዴኤታው የተናገሩት።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025