ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ።
"ህገወጥነትን መከላከልና የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት" በሚል መሪ ሃሳብ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሰባት ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ደብረብርሀን ከተማ እየተካሄደ ነው።
የቢሮው ሃላፊ ኢብራሂም መሐመድ(ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግስት በስምንት ዋና ዋና ከተሞች አንደኛ ደረጃ የገበያ ማዕከላት ግንባታ እያካሄደ ይገኛል።
እንዲሁም 15 ሁለተኛ ደረጃ የገበያ ማዕከላት በሌሎች የክልሉ ከተሞች ግንባታቸው መጀመሩን ተናግረዋል።
የገበያ ማዕከላቱ መገንባት ህገ ወጥ ንግድና ደላlaን በመከላከል የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርትን ከአምራቹ በቀጥታ በመረከብ ለሸማቹ እንዲደርስና ገበያን ለማረጋጋት እንደሚያግዙ ተናግረዋል።
ማዕከላቱ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ በየደረጃው የሚገኙ አመራር አባላትና የዘርፉ ባለሙያዎች ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት፤ ገበያን ለማረጋጋት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ ይርጋለም ምስጋናው በበኩላቸው፤ በበጀት ዓመቱ 49 ሚሊየን ብር በመመደብ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚው ማቅረብ ተችሏል።
የኑሮ ውድነትን ለመቀነስም አምራችና ሸማቹን በቀጥታ የሚያገናኝ የመጀመሪያ ደረጃ የገበያ ማዕከል ግንባታ በ196 ሚሊየን ብር ወጪ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።
በመድረኩ ላይ ከክልል፣ ከዞንና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ንግድና ገበያ ልማት ዘርፍ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ነው።
ተሳታፊዎቹ ቀደም ሲል በደብረብርሃን ከተማ ገበያን ለማረጋጋት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ተመልክተዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025