የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በክልሉ በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ማፍለቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል

Jan 13, 2025

IDOPRESS

ሆሳዕና ፡ ታህሳስ 26/2017(ኢዜአ):- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችና ምርጥ ዘር ማፍለቅ ላይ ትኩረት መሰጠቱ ተገለጸ።

በክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በግብርናው ዘርፍ ያሉ ፀጋዎችንና ማነቆዎችን በመለየት ችግር ፈቺ የምርምር እቅድ ማዘጋጀት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።


በመድረኩ ላይ የተገኙት በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር ፤ በክልሉ በግብርና ዘርፍ ያለውን አቅም ለመጠቀም ማዘመን ይገባል ብለዋል ።

በግብርናው ዘርፍ ያሉ ዕድሎችን በአግባቡ ለመጠቀም በጥናትና ምርምር ማስደገፍ ተገቢ መሆኑን አመልክተዋል።

ይህም ዕድሎችን ወደ ውጤት በመቀየር ከቤተሰብ እስከ ማህበረሰብ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል ።

በክልሉ ግብርናን በማዘመን በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት እየተደረገ የሚገኘውን ጥረት በማገዝ ተመራማሪዎች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለባቸወም ገልጸዋል።

የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ ተረፈ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ በክልሉ የሚከናወኑ የግብርና ልማት ስራዎች በምርምር የታገዙ እንዲሆኑ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችና ምርጥ ዘር ማፍለቅ እንዲሁም በሂደት የሚገጥሙ የተባይና መሰል በሽታ ቁጥጥር ላይ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።

በክልሉ በዘርፉ ባሉ ማነቆዎች ላይ ጥናት መካሄዱን ጠቅሰው፤ በዚህም ለተለዩ ማነቆዎች የመፍትሄ ሃሳቦችና የቀጣይ እርምጃዎች ላይ በአሁኑ መድረኩ ውይይት እንደሚደረግበት አመልክተዋል።

የክልሉ ፣ የዞንና የልዩ ወረዳ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራር አባላት በውይይት መድረኩ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.