የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ የልማት ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ አጠናቆ ስራ ለማስጀመር እየተሰራ ነው - አቶ ኦርዲን በድሪ

Jan 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 3/2017(ኢዜአ)፡- በሀረሪ ክልል የልማት ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ አጠናቆ ስራ ለማስጀመር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

አቶ ኦርዲን በድሪ በሀረር ከተማ በ1 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ላይ ግንባታው እየተካሄደ የሚገኘውን የአባድር ፕላዛ ፕሮጀክት ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመስክ ምልከታው ላይ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ ጥሩ በሚባል የግንባታ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን አመላክቷል።


በክልሉ የልማት ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ በጥራት እና ፍጥነት ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ አጠናቆ ስራ ለማስጀመር እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

በተለይ በቅርቡ ተቋቁሞ ወደ ስራ የገባው የሀረሪ ኮንስትራክሽን እና መሰረተ ልማት ግንባታ ድርጅት የፕሮጀክት ግንባታ ስራዎችን በምሽት ጭምር በማከናወን የልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ ማስቻሉን ገልፀዋል።

ድርጅቱ በግል የኮንስትራክሽን ድርጅቶች በስራ መደራረብ ምክንያት በፕሮጀክቶች ላይ ይስተዋል የነበረውን መዘግየት በማስቀረት ጥሩ ተሞክሮ እና ልምድ የተወሰደበት መሆኑንም ጠቁመዋል።


አክለውም ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት ግዜን በአግባቡ በመጠቀም አመራሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ከግንባታ ስራው ጎን ማከናወን እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በሌላ በኩል በክልሉ ግንባታቸው ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ ህንፃዎችን በፍጥነት ወደ ስራ ማስገባት እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ አስገንዝበዋል።

በ1 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ላይ እየተገነባ የሚገኘው የአባድር ፕላዛ ግሪነሪ፤ አንፊ ቲያትር፤ ፋውንቴኖች እና ሌሎች መናፈሻዎችን የያዘ መሆኑ ተመላክቷል።

በመስክ ምልከታው የክልሉ ካቢኔ አባላት መገኘታቸውንም ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.