የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የካፒታል ገበያ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ገበያ መሪ ተዋናይ እንድትሆን ያስችላታል - የናይጄርያ ኤክስቼንጅ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተሚ ፖፖላ

Jan 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 3/2017(ኢዜአ)፡- የካፒታል ገበያ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ገበያ መሪ ተዋናይ እንድትሆን ያስችላታል ሲሉ የናይጄርያ ኤክስቼንጅ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተሚ ፖፖላ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን ትናንት በይፋ አስጀምረዋል፡፡


የናይጄርያ ኤክስቼንጅ ግሩፕ ሥራ አስፈፃሚ ተሚ ፖፖላ በመርሀ ግብሩ ወቅት በሰጡት ማብራሪያ በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መጀመር በአፍሪካ ገበያ የጎላ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

በናይጄርያ ከ62 አመት በፊት የተጀመረው የካፒታል ገበያ በተወሰነ ዘርፍ ላይ ከማተኮር ወጥቶ አማራጭ ገበያ እያፈላለገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ድርሻ በመሳተፋቸው መደሰታቸውን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ ዘርፉ ሁሉንም በንቃት በማሳተፍ ምርትና አገልግሎቶችን በስፋት ማቅረብ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መንግሥት ምቹ ፖሊሲዎችና አሰራሮችን በመዘርጋት ለመሰረተ ልማት ማስፋፊያ የሚሆን ገቢ መሰበሰብ የግሉ ዘርፍ ደግሞ የተፈጠረለትን እድል በመጠቀም ገበያውን በስፋት መቀላቀል አለበት ብለዋል፡፡

በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል ያለው ትብብር መጎልበት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመቋቋም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን የሚያስቀጥል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዓለም ላይ ያለ የካፒታል ገበያ ውጤታማ ኢኮኖሚ መገንባት አስቸጋሪ መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ ስኬት ላይ ለመድረስ የሌሎች ሀገራትን ልምድ መውሰድ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡


የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለሥራ እድል ፈጠራ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ገንቢ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ገበያው ኢትዮጵያን በአፍሪካ ገበያ መሪ ተዋናይ መሆን የሚያስችል አቅም እንደሚፈጥርላት እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.