አዲስ አበባ፤ጥር 6 /2017(ኢዜአ)፡-የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ።
6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አራተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው።
በዚሁ ጊዜ የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ የቀረበ ሲሆን የምክር ቤቱ አባላት በአዋጁ ላይ ያላቸውን ጥያቄ እና አስተያየት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጅጌ(ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ በኢትዮጵያ ከሚመነጨው ሀብት አኳያ የሚሰበሰበው ገቢ በቂ አለመሆኑን ገልጸዋል።
በታክስ የሚሰበሰበው ገቢ ለጥቅል አገራዊ ምርት (ጂ ዲ ፒ) ያለው አስተዋጽኦ ከ7 በመቶ እንደማይበልጥ ጠቅሰው ይህም ከሳሃራ በታች ካሉ ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ መሆኑን አብራርተዋል።
ገቢ የመሰብሰብ አቅም ሊያድግ እንደሚገባ የገለጹት ሚኒስትሩ አዋጁ ታክስ የመሰብሰብ አቅምን የሚያሳድግ መሆኑን ተናግረዋል።
አዋጁ የታክስ መሰረትን ለማስፋት፣ የመንግሥት መሰረተ ልማት አቅርቦት አቅምን ለማሳደግ እንዲሁም ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመተግበር አጋዥ መሆኑን አመላክተዋል።
አንገብጋቢ ለሆኑ የሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የገቢ አቅምን ማሳደግ ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልጸው፤ ለዚህም የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጁ ሥራ ላይ መዋል የላቀ ፋይዳ አለው ብለዋል።
ምክር ቤቱ በንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጁ ዙሪያ በቀረቡ ጥያቄና አስተያየቶች ላይ ከተወያየ በኋላ አዋጁን መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025