የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

<p>ኤሌክትሮኒክ ቲኬት የመናኸሪያ አገልግሎት አሰጣጥን ምቹና ቀልጣፋ አድርጓል</p>

Jan 18, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2017(ኢዜአ)፦ በሀዋሳ ከተማ መናኸሪያዎች የተተገበረው ኤሌክትሮኒክ ቲኬት የመናኸሪያ አገልግሎት አሰጣጥን ምቹና ቀልጣፋ እንዲሆን ማስቻሉን የሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በሐዋሳ ከተማ መናኸሪያዎች አገልግሎትን ለማዘመን የተተገበሩ ዘመናዊ አሰራሮችን ተመልክተዋል።

የሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምሩ ታፌ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት፤ የትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን የመናኸሪያዎችን ደረጃ የማሻሻልና በቴክኖሎጂ የማስደገፍ ሥራ እየተከናወነ ነው።

የመናኸሪያዎችን የትኬት አገልግሎት ፈጣን፣ ምቹና ቀልጣፋ ለማድረግ የኤሌክትሮኒክ ወይም ኢ-ትኬት ሥርዓት መተግበሩን ጠቅሰዋል።

ይህም ከታሪፍ በላይ ማስከፈል፣ ትርፍ መጫን፣ ከተመደቡበት የስምሪት መሥመር ውጪ መጫንና መሰል የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን መቅረፉን ገልጸዋል።

በቀጣይም ከሐዋሳ ከተማ ተሞክሮን በክልሉ ዞኖች እና ወረዳዎች ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.