ጋምቤላ፤ ጥር 9/2017(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም በማሻሻል የማህበረሰቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ገለጸ።
አስተዳደሩ በክልሉ ከ10 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ እየተገነቡ በሚገኙ ዘጠኝ የመንገድ ፕሮጀክቶች ዙሪያ ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ተወያይቷል።
የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀመድ አብዱራህማን በውይይቱ ላይ እንደገለጹት አስተዳደሩ ውስጣዊ አሰራሮችን በማጠናከርና የፕሮጀክት ፈፃሚዎችን በማትጋት የመንገድ ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ለማሻሻል በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።
በክልሉ በሂደት ላይ የሚገኙትን የመንገድ ፕሮጀክቶች በማፋጠንና ተጀምረው በአፈፃፀም ችግር የተቋረጡትን በማስቀጠል ለህዝቡ የመንገድ መሰረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በትጋት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
አስተዳደሩ በክልሉ እያከናወናቸው ለሚገኙት የመንገድ ፕሮጀክቶች ስኬታማነት የክልሉ መንግስት ድጋፍና ትብብር እንዲጠናከር ዋና ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ዓለሚቱ ኡሞድ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ክልሉ ቀደም ሲል በነበሩት ዓመታት የተፈለገውን ያህል የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽ ሳይሆን ቆይቷል።
ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የክልሉን ህዝብ የመንገድ መሰረተ ልማት ጥያቄዎች ለመፍታት በፌዴራል መንግስት የተጀመሩት ስራዎች የሚበረታቱ ቢሆንም በተወሰኑ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ የአፈፃፀም ችግሮች መኖራቸውን ገልጸዋል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በክልሉ በሂደት ላይ የሚገኙ መንገዶች ግንባታን ለማፋጠንና የተቋረጡትን ለማስቀጠል የክልሉ መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የእቅድና ፕሮግራም አስተዳደር ዳይሬክተር ወይዘሮ ቆንጅት ዓለሙ በመድረኩ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት በክልሉ ከ10 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ ዘጠኝ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጀምረው እንደነበር ተናግረዋል።
ከ580 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ካለቸው ዘጠኝ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል አምስቱ በግንባታ ሂደት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው ቀሪዎቹ በአፈፃፀም ችግርና በሌሎች ምክንያቶች መቋረጣቸውን ገልጸዋል።
በግንባታ ሂደት ላይ ከሚገኙት ፕሮጀክቶች መካከል ከጋምቤላ አቦቦ ፑኝውዶ፣ ከፑኝውዶ ጊሎ ራድ፣ ከላሬ ጂካዎ፤ ከፑኝውዶ ጆር አንጌላ ሲሆኑ ከተቋረጡት ፕሮጀክቶች መካከል ደግሞ ከኮኮሪ -መንገሺ- ሜጢ- ኩቢጦ፣ከጋምቤላ ኢሊያ፣ ከኢሊያ መኮይና ሌሎች እንደሚገኙበት ተናግረዋል።
በዘንድሮው ዓመት በሂደት ላይ ከሚገኙት ፕሮጀክቶች መካከል ሁለቱን ለማጠናቀቅና በሂደት ላይ ያሉትን ደግሞ ለማፋጠን እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የተቋረጡትን ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025