የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

<p>የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪ ዘርፉን አነቃቅቷል- አቶ ኦርዲን በድሪ</p>

Jan 18, 2025

IDOPRESS


ሐረር፤ ጥር 10/2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በሐረሪ ክልል የኢንዱስትሪ ዘርፉን ማነቃቃቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ።

የኢትዮጵያ ታምርት ክልል አቀፍ ንቅናቄ መድረክ በሐረሪ ክልል እየተካሄደ ነው።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በክልሉ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ መነቃቃት ተፈጥሯል።

በተለይ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚታዩ ማነቆዎችን በመፍታት ምርታማነት እንዲያድግ ማስቻሉን ገልጸዋል።

በንቅናቄው ተዘግተው የነበሩ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ መመለሳቸውን ጠቅሰው በክልሉ የሚገኙ አነስተኛ ኢንዳስትሪዎች ወደ መካከለኛ፤ መካከለኛዎቹ ደግሞ ወደ ከፍተኛ ኢንዳስትሪ እንዲሸጋገሩ ዕድል መስጠሩንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ስኬታማ እንዲሆን የክልሉ መንግስት በዘርፉ ለተሰማሩት አካላት ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰው የተጀመረው አበረታች ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስገንዝበዋል።


የሐረሪ ክልል ኢንተርፕራይዝ ልማትና ኢንዳስትሪ ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማኢል ዩስፍ በበኩላቸው በክልሉ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ በምግብና መጠጥ ማቀነባበር፣ በእንጨትና ብረታ ብረትና በሌሎች የተሰማሩ አምራቾች እየተበራከቱ ነው ብለዋል።

በዚህም በክልሉ 165 አነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዳስትሪዎች በተለያዩ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው የማምረት ስራ እያከናወኑ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።

በተለይ አምራች እንዳስትሪው የማምረት አቅማቸውን የማጎልበትና የሚገጥማቸውን ችግር የመቅረፍ ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

"ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት" በሚል መሪ ሃሳብ በተዘጋጀው ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ አመራር አካላትና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.