የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

<p>በሀረሪ ክልል ከ13ሺህ ሊትር በላይ በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ነዳጅ ተያዘ</p>

Jan 21, 2025

IDOPRESS

ሀረር፤ጥር 12/2017(ኢዜአ):- በሀረሪ ክልል በአንድ ወር ግዜ ውስጥ 13 ሺህ 480 ሊትር ነዳጅ መያዙን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን እንዳሉት፥ በክልሉ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን ለማስቆም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በተሰራው ስራ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 13ሺ 480 ሊትር ነዳጅ ከነተጠርጣሪዎቹ መያዙን ጠቁመዋል።

ነዳጁ የተያዘው በኬላዎች ላይ በተደረገ ፍተሻ እንዲሁም ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በሕገ ወጥ መንገድ በቤት ውስጥ ተከማችቶ የተገኘ መሆኑን ገልጸዋል።


ነዳጅን በበርሜል በህገ ወጥ መንገድ ሲያሸሹ የተደረሰባቸው እና በመኖሪያ ቤታቸው ደብቀው የተገኙ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

መንግስት ከፍተኛ በጀት መድቦ የሚያስገባው ነዳጅ ለታለመለት አላማ ሊውል ይገባል ያሉት ኮሚሽነሩ፥ በህገወጥ የነዳጅ ግብይት በሚሳተፉ አካላት ላይ በቀጣይም የተጠናከረ ክትትል በማድረግ አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል።

በቀጣይም ሕገ ወጥ ነዳጅን ጨምሮ ሌሎች ሕገ ወጥ ተግባራትን ለመከላከል የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉም ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን ጠቁመዋል።

ማህበረሰብ በአካባቢው ሕገ ወጥ የነዳጅ ግብይትን ሲመለከት በአካባቢው ለሚገኙ የፖሊስ ጽ/ቤት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.