አዲስ አበባ፣ ጥር 12/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት ሁለንተናዊ ሀገራዊ ብልጽግና ዕውን ለማድረግ በመንግስት የተወሰዱ ተግባራዊ እርምጃዎች ማህበራዊ አካታችነትን እያረጋገጡ መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር) ገለፁ።
ሚኒስትሯ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ሥዩም አዘጋጅነት በሚቀርበው ‘ኢትዮጵያ ኢን ፎከስ’ በተሰኘው ፕሮግራም ላይ ቀርበው በተለይም ገቢራዊ የተደረጉ ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች ከማህበራዊ አካታችነት አኳያ በነበራቸው ሚና ዙሪያ አብራርተዋል።
ሁለንተናዊ ብልጽግና ከዘላቂ ልማት ግቦች ተለምዷዊ ብያኔዎች የተሻገረ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ አንድምታዎች እንዳሉት ሚኒስትሯ ጠቅሰዋል።
ሁለንተናዊ ብልጽግና በልቶ ከማድር ያለፈ ደስተኛ ሕይወት፣ ማህበራዊ ዋስትና የማረጋገጥ፣ ክብር እና መሻትን ዕውን የማድረግ፣ በምቹና ተስማሚ አካባቢ የመኖር፣ አካታችነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥና መሰል ጽንሰ ሃሳቦችን እንደሚያቅፍ ጠቅሰዋል።
ከዚህ አካያ ባለፉት ዓመታት ሁለንተናዊ ብልጽግናን እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ማህበረሰብ ለማሳካት በተወሰዱ እርምጃዎች በሁሉም መስኮች አካታችና አሳታፊ ዕድገት በማስመዝገብ ማህበራዊ አካታችነትን ማረጋገጥ እንዳስቻለ ጠቁመዋል።
ይህን ስኬት ዕውን ለማድረግ ደግሞ መንግስት የሀገርን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎችን ቀይሶ ገቢራዊ ማድረጉን አውስተዋል።
ከድህነትን ቅነሳ ትርክትና ግብ ከማስቀመጥ ባሻገር ገቢራዊ የተደረጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች በሁሉም መስክ ማሀበራዊ አካታችነትን ዕውን ከማድረግ ረገድ ተግባራዊና ተጨባጭ ለውጥ አምጥተዋል ብለዋል።
በተለይም ከድህነት አዙሪት ለማላቀቅ የሀገርን ጸጋ የማየትና አቅምን አሟጦ በመጠቀምና በማልማት ሀገራዊ መሻትን ዕውን ያደረጉ እመርታዊ ለውጦች ተመዝግበዋል ነው ያሉት።
ለአብነትም በትምህርትና ጤና ዘርፍ ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር የተጣጣሙ ሁሉንም ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ተደራሽና ጥራት ያለው የጤና እና የትምህርት አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የፖሊሲ እርምጃዎች ተተግብረዋል ብለዋል።
በጤናው መስክ ከማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ጀምሮ አካታች የጤና አገልግሎት፣ በትምህርት ረገድም ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ የተሰሩ ሁሉን አቀፍ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማሻሻያዎች አበረታች ውጤቶች እያስገኙ መሆኑን ጠቁመዋል።
በአካታች ፋይናንስ ረገድም ከገጠር እስከ ከተማ አካታች የፋይናንስ ስርዓት ለመዘረጋት የተሄደውን ርቀት አውስተዋል።
በድህነት ቅነሳ ረገድ ሰው ተኮር ፖሊሲዎች በመቅረፅ ዜጎች ከድህነት ተላቀው የምግብ ዋስትናን እንዲያረጋግጡ አስቻይ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል።
ባለፉት ስድስት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ ቀዳሚ ትኩረት ተሰጥቶ ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን ማሳያዎችን በመጥቀስ አስረድተዋል።
ይኼውም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑትን ጨምሮ አንድ ቢሊዮን ኩንታል ሰብል ምርት መመረቱን አንስተዋል።
በተለይም የስንዴ ልማት ኢኒሼቲቭ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ ያደረገና እንደ ሀገር ራስን ያስቻለ ብቻ ሳይሆን ስንዴ ወደ ውጭ መላክ የተበሰረበት ስኬት መመዝገቡን አውስተዋል።
የግብርና ፖሊሲዎች በቴክኖሎጂ በታዘገ አነስተኛ መስኖ፣ በከተማ ግብርና፣ በኩታገጠም እርሻና መሰል መርሀ ግብሮችን በመተግበር የአምራቾች ሕይወትና ኑሮ እንዲለወጥ ያስቻሉ እንደሆኑ አንስተዋል።
ይህም የምግብ ዋስትና እና ስርዓተ ምግብ ሽግግርን በማረጋገጥ ወደ ሁለንተናዊ ብልጸግና የሚያሸጋገር ወሳኝ እርምጃ እንደነበር ነው የጠቀሱት።
በሰብል ምርትና ምርታማነት ብቻ ስርዓተ ምግብን ማረጋገጥ እንደማይቻል ጠቅሰው፤ በዚህም የእንስሳት ሀብትን በማመዘንና ምርታማነትን በመጨመር የአመጋግብ ስርዓትን ማሻሻል እንደሚያሻ ጠቁመዋል።
በዚህም በማር፣ በስጋ፣ በወተትና በእንቁላል ምርታማነት በመጨመር ስርዓተ ምግብን ለመለወጥ የተተገበረውን የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ውጤታማነት ጠቅሰዋል።
በስርዓተ ጾታ፣ በከተማ ቤቶች ልማት፣ በመሰረተ ልማት፣ በዲጂታል ኢኮኖሚና በፋይናንት ተቋማት በኩል የተወሰዱ ሪፎርሞችም ማህበራዊ አካታችነት ያረጋገጡና የሀገርን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ መሰረት ስለመጣላቸው አንስተዋል።
በሌላ በኩል በሁሉም መስኮች የመንግስትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ከወትሮው በተለዬ አዲስ መልክ ይዞ ለማህበራዊ አካታችነት መረጋገጥ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ያለበት ወቅት ነው ብለዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025