አዳማ፤ ጥር 13/2017(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ከ750 ሺህ በላይ ዘመናዊ የንብ ቀፎ ለአርሶ አደሮችና ለማህበራት መሰራጨቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለፀ።
በቢሮው የእንስሳት ሀብት ልማት ዳይሬክተር አቶ ደምሴ ኩምሣ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በክልሉ የማር ልማት እንሼቲቭ ተቀርጾ ባለፉት ሶስት ዓመታት ሲሰራ ቆይቷል።
ዘንድሮ በክልሉ የማር ምርትን ለማሳደግ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዘመናዊ የንብ ማነቢያ ቀፎ ለማሰራጨት ታቅዶ ባለፉት ስድስት ወራት ከ750 ሺህ በላይ መሰራጨቱን ተናግረዋል።
ኢንሼቲቩ በምዕራብ ኦሮሚያ በተለይ በጂማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉ አባቦር፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቄሌም ወለጋና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋን ጨምሮ በክልሉ 15 ዞኖች እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰዋል።
አሁን ላይ በክልሉ የተለያዩ ዞኖች የማር ልማት ስራ በአርሶና አርብቶ አደሮች እንዲሁም በወጣቶች እየተከናወነ እንደሆነም ገልጸዋል።
አምና ከ1 ሚሊዮን በላይ ዘመናዊ የንብ ቆፎ ማሰራጨት መቻሉን አስታውሰው፤ ዘንድሮም የንብ ቀፎዎቹ ለአርሶና አብርቶ አደሮች እንዲሁም በማህበር ለተደራጁ ወጣቶች ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑን አክለዋል።
በክልሉ የማር ምርት በዓመት ሁለት ጊዜ እንደሚሰበሰብ ጠቁመው በዚህ ወቅት የመጀመሪያው በጋ ወቅት የማር ምርት እየተሰበሰበ ሲሆን ቀጣይ ግንቦትና ሰኔ ሁለተኛው ምርት የሚሰበሰብበት መሆኑን ተናግረዋል።
በማር ምርት ዘመናዊ የንብ ማነቢያ ቀፎን ጨምሮ የማር ምርት ማጥለያ፣ ማርና ሰም መለያ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ጥራት ያለው ዘመናዊ ቀፎ ከክልሉ ደን ልማትና ዱር እንስሳት ኢንተርፕራይዝ ጋር በትብብር እየተመረተ መሆኑንም ገልጸዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025