የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

<p>ለባሕር ዳር ከተማ ኢንቨስትመንት መጎልበት ባለሀብቱ ሚናውን ሊወጣ ይገባል</p>

Jan 22, 2025

IDOPRESS

ባሕር ዳር፤ ጥር 13/2017(ኢዜአ)፦ ባሕር ዳር ከተማን ተመራጭ የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ባለሀብቶች በሰላም ማስጠበቅ እና ልማት ላይ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የከተማዋ አስተዳደሩ ጥሪ አቀረበ።

በባሕር ዳር ከተማ ልማትና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ዛሬ ተካሄዷል።

የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው እንደገለጹት፤ ከተማ አስተዳደሩ ከወትሮው በተለዬ ከተማዋን ለማልማት እየሰራ ነው።

በዚህም የከተማዋን ሰላምና ነዋሪዎችን ደህንነት ከማረጋገጥ በተጓዳኝ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ስራዎች እየተቀላጠፉ ነው ብለዋል።

ሰፋፊ የአስፋልት መንገዶች፣ ስማርት ሲቲ፣ የዲጂታላይዜሽን እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ግንባታዎችን ለአብነት ጠቅሰዋል።

ትውልድ ተሻጋሪ ፋይዳ ያለው የከተማዋ ኮሪደር ልማትም ዘላቂና ምቹ የኑሮና የስራ ከተማ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑንም እንዲሁ።

ሁሉን አቀፍ የከተማ ልማት ጥረቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ባለሃብቱ የሚጠበቅበትን ወሳኝ ሚና በመረዳት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጠይቀዋል።

ከተሳታፊ ባለሃብቶች መካከል አቶ እንግዳው ወርቁና አቶ ማስተዋል አያልነህ የኮሪደር ልማቱን ጨምሮ ምቹና ዘመናዊ ከተማ ግንባታ ፕሮጀክቶችን አድንቀዋል።

በመሆኑም የመንግስትን ጥረት በመደገፍ ከተማን ለኢንቨስመንት ተወዳዳሪ እንድትሆን በባለቤትነት ስሜት እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል።

በከተማዋ የተጠናቀቁ የልማት ፕሮጀክቶችን መገብኘታቸውን ገልጸው፤ የልማት ስራዎችን ከመጠበቅና ከመንከባከብ ባሻገር አዳዲስ የልማት ስራዎችን በመደገፍ የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.