ደሴ ኢዜአ ጥር 28/2017-- በደቡብ ወሎ ዞን በዘንድሮው የበልግ ወቅት ከ104 ሺህ 600 በላይ ሄክታር መሬት እየታረሰ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ ይመር ሰይድ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አርሶ አደሩ የሰብል ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ በትኩረት እየተሰራ ነው።
በዘንድሮው የበልግ ወቅት ከ104 ሺህ 600 ሄክታር የሚበልጥ መሬት እየታረሰ ሲሆን፤በሚቀጥለው ወር የዘር ስራ እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡
በበልግ ወቅቱ ከሚለማው መሬት ከሁለት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማምረት መታቀዱንም ነው የተናገሩት።
ምርታማነትን ለማሳደግም ከሁለት ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያን ጨምሮ የፋብሪካ ማዳበሪያም ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ተደርጓል ብለዋል።
በዞኑ ለጋምቦ ወረዳ የቀበሌ 14 ነዋሪ አርሶ አደር በላይ አህመድ፤ በአንድ ሄክታር ተኩል መሬት ላይ ገብስ፣ ስንዴና ጤፍ ለማልማት የእርሻ ሥራ አጠናቀዋል፡፡
ከሚያለሙት መሬትም ከ30 ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠብቁ ጠቁመው፤ ባለፈው ዓመት ከዚህ መሬት 26 ኩንታል ምርት ማግኘታቸውን አስታውሰዋል።
የበልግ ዝናብ ምርታማነትን በማሳደግ ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን የተናገሩት ሌላው የደሴ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደር ከድር ሙሄው ናቸው።
በዘንድሮ የበልግ ወቅትም አንድ ሄክታር መሬት በገብስ፣ ስንዴና ባቄላ ዘር ለመሸፈን የእርሻ ስራ በማጠናቀቅ የዝናቡን መጣል እየተጠባበቁ ይገኛል፡፡
ከልማቱ ከ20 ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ ማዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡
በዞኑ ባለፈው ዓመት በበልግ ወቅት ከለማው 105 ሺህ ሄክታር መሬት 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን ከመምሪያው የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025