አክሱም፤ ጥር 29/2017 (ኢዜአ)፦ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ በምርምር ያወጣቸውን የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለአርሶ አደሮች እያስተዋወቀ መሆኑን ገለጸ።
በዩኒቨርሲቲው የመካኒካልና ኢንዳስትሪያል ምህንድስና ትምህርት ከፍል መምህር ገብረሚካኤል ገብረማርያም ለኢዜአ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በምርምር እያወጣ ነው።
ለአብነትም "በዲናሞ" እና በሰው ሃይል ጉልበት የሚሰሩ የሰብል መዝርያ፣ ማጨጃና መውቂያ ማሽኖችን ጠቅሰዋል።
ከወዳደቁ ቁሳቁሶች የተሰሩት የግብርና ቴክኖሎጂዎች ገብስ፣ ሰንዴና ሌሎች ሰብሎችን በመስመር መዝራት፣ ማጨድ፣ መሰብሰብና መውቃት የሚያስችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሌላው በትምህርት ክፍሉ መምህር ገብረሚካኤል ገብረመድህን በበኩላቸው የወዳደቁ ብረታ ብረቶችን በመጠቀም በአንድ ጊዜ በአራት መስመሮች ሰብልን መዝራት የሚያስችል ማሽን መስራታቸውን ገልጸዋል።
ቴክኖሎጂው ዘርን ከብክነት ከመከላከል አልፎ የአርሶ አደሩን ጉልበትና የሥራ ጊዜን የመቆጠብ አቅም እንዳለው ጠቁመዋል።
ዩኒቨርሲቲው የግብርና ቴክኖሎጂዎቹን ለአርሶ አደሮች እያስተዋወቀ መሆኑን ምሁራኑ አስታውቀዋል።
ኢዜአ ካነጋገራቸው አርሶ አደሮች መካከል ተክለወይኒ ገብረስላሴ፣ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የሰራው ዘመናዊ ማጭድ በጠባብ የእርሻ ማሳ ሰብልን በአጭር ግዜ ለመሰብሰብ ምቹ መሆኑን ገልጸዋል።
"በዲናሞ" የሚሰራ የማረሻ ማሽን የሰውን ጉልበት እንደሚቆጥብ በተግባር ማረጋገጣቸውን የተናገሩት ደግሞ አርሶ አደር ሃፍተወልድ መኮንን ናቸው።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025