አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው “Leadership in Connecting Africa through Transport Award” የተሰኘ አህጉራዊ ሽልማት አግኝተዋል።
በአፍሪካ አህጉር ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና ላይ ያተኮረ ዓመታዊ የ“2025 የአፍሪካ ፕሮስፔሪቲ ዲያሎግ” በጋና አክራ ተካሂዷል።
በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው አፍሪካን በአየር ትራንስፖርት በማገናኘት ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እየተጫወተ ላለው ሚና ላሳዩት የላቀ የአመራርነት ሚና የ“Leadership in Connecting Africa through Transport Award” ተሸላሚ ሆነዋል።
ሽልማቱ አፍሪካን እርስ በእርስ በማገናኘት ቁርጠኛ የአመራርነት አስተዋፅዖ ላበረከቱ ግለሰቦች ዕውቅና የሚሰጥበት መሆኑን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የ“2025 የአፍሪካ ፕሮስፔሪቲ ዲያሎግ” ላይ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የታላላቅ አህጉር ዓቀፍ የንግድ ተቋማት መሪዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተገኝተዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025