አዲስ አበባ፤ጥር 29/2017(ኢዜአ)፦በተያዘው ዓመት አምስት የሚደርሱ ኩባንያዎችን ወደ አክሲዮን ገበያው ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን እስማኤል(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የተለያዩ የንግድ አይነቶችን ታሳቢ በማድረግ ሶስት ልዩ ልዩ የገበያ አይነቶችን የሚያቀርብ ነው፡፡
እነርሱም የአክሲዮን ገበያ፣ የዕዳ ሰነድ ገበያ እና የአማራጭ ገበያ ናቸው፡፡
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን እስማኤል(ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት ተቋሙ ዓለም ላይ ካሉ የካፒታል ገበያ ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚያስችለውን የሕግ ማዕቀፍና አስፈላጊ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን አሟልቶ ወደ ሥራ ገብቷል።
አሁን ላይ አንድ የግል ባንክ በገበያው ለመሳተፍ መመዝገቡን ጠቅሰው፤ በቀጣይም ኢትዮ - ቴሌኮምን ጨምሮ አምስት ኩባንያዎችን እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን ይቀላቀላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።
በገበያው የተለያዩ የፋይናንስ ውጤቶችንም የማስተዋወቅ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸው፤ ይህንንም ተከትሎ የሀገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎች ለማሳተፍ ፍላጎት እያሳዩ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም በኢትዮጵያ በባንኮች መካከል ያለው የገንዘብ ገበያና የዕዳ ሰነድ ገበያው ፍላጎቱ እንዲጨምር ማድረጉን አስረድተዋል።
በቀጣይ ስድስት ዓመታትም 50 የሚሆኑ ኩባንያዎችን ወደ ገበያው በመቀላቀል የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ላይ ካሉ የተሻሉ ተቋማት ተርታ የማሰለፍ እቅድ መኖሩን አስረድተዋል።
ይህንንም ርዕይ እውን ለማድረግ የቁጠባ ባህላቸው ያደገ እንዲሁም ሀብት በማሰባሰብ ኢንቨስት የሚያደርጉ ተቋማት የተከማቹባቸው አገራትን ትኩረት ያደረገ ገበያውን የማስተዋወቅ ሥራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ለአብነትም ደቡብ አፍሪካ፣ ለንደን፣ ዱባይና ኒውዮርክ ላይ ትኩረት ያደረጉ ገበያውን የማስተዋወቅ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ከካዛብላንካ፣ ከናይሮቢና ከናይጄሪያ የካፒታል ገበያ ጋር አጋርነት እንዳለው ገልጸው፣ የአፍሪካና የምስራቅ አፍሪካ የካፒታል ገበያ ማኅበር አባል መሆኑን ጠቅሰዋል።
ይህም የተቋሙን ውጤታማነትና ተወዳዳሪነት እንዲሁም በፈጠራ የታከለ ገበያ ለመገንባት አቅም እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
ገበያው ከዓለም አቀፍ የዘርፉ ኢንዱስትሪ ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚያስችል አጠቃላይ የካፒታል ገበያን ሥነ-ምህዳር የማስተካከል ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025