የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

<p>የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የድሮን ባለሙያዎችን አስመረቀ</p>

Feb 8, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በድሮን ታክቲካል አጠቃቀም ላይ ያሰለጠናቸውን የፖሊስ እና የሪፐብሊካን ጋርድ የድሮን ባለሙያዎችን አስመርቋል።

ስልጠናው የሰጡት የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የዱባይ ፖሊስ ኦፊሰሮች ናቸው።


የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ለሚኒስቴሩ እና ለዱባይ ፖሊስ ምስጋና አቅርበዋል።

ስልጠናው የፖሊስ መኮንኖችን ሙያዊ ኃላፊነት ለመወጣት ያላቸውን አቅም እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ በሚካሄደው የ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የዝግጅቱን ደህንነት ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።

ኮሚሽነር ጀነራሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና የሪፐብሊካን ጋርድ የድሮን ባለሙያዎች ያገኙትን ዕውቀት ለተፈለገው ዓላማ በማዋል በከፍተኛ ሙያዊ ዲስፕሊን በብቃት እንዲወጡ አሳስበዋል።


በተጨማሪም የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የዱባይ ፖሊስ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ላደረጉት ሙያዊና የሎጂስቲክስ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ድጋፉ የፖሊስ ሰራዊቱ ተልዕኮውን በተሳካ ሁኔታ እንዲፈጽም ከፍተኛ ሚና አንዳለው መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.