
አዲስ አበባ፤ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ወራት የከተማዋን ገጽታ የቀየሩና የህዝቡን የልማት ጥያቄ የመለሱ ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
አስተዳደሩ የ2017 በጀት ዓመት የመንግስት እና የፓርቲ የስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል።
በዚሁ ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ባለፉት ስድስት ወራት በሁሉም ዘርፎች አመርቂ አፈጻጸሞች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
በአስተዳደሩ የዕቅድ አፈጻጸም አጠቃላይ ደረጃ 90 በመቶ መድረሱን ጠቁመው፥አፈጻጸሙ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ከህዝቡ በተሰበሰበው ገቢ ህዝቡን ተጠቃሚ ከማድረግ እና ዘላቂ ልማትን ከማረጋገጥ አኳያ አርዓያ የሚሆኑ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።
ከዚህ አንጻር በመዲናዋ ባለፉት ስድስት ወራት ዘላቂ ልማትንና የህዝብ ተጠቃሚነትን ያረጋገጡ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡
አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹና ውብ የሆነች ከተማ ለማድረግ በመልሶ ግንባታ እና በመሠረተ ልማት ማስፋፋት የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውንም ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል።
የከተማዋን ዘላቂ ልማት በተሟላ ሁኔታ ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ጥረቶች ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማን ዘላቂ ሰላም ማስጠበቅ መቻሉን ተከትሎ የቱሪዝም ፍሰቱ መጨመሩን ጠቁመዋል፡፡
በስድስት ወራቱ የተመዘገቡ አፈጻጸሞችና የተገኙ ውጤቶች ከከተማዋ የልማት ፍላጎት አንጻር በቀጣይ በርካታ ስራዎች እንደሚከናወኑ የሚያረጋግጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
በቀጣይ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የተጀመሩ ውጤታማ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ጠቁመዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ አደም ኑሪ ባቀረቡት ሪፖርት፤ የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ከእጅ ንክኪ ነጻ ከማድረግ አንጻር ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት በመዲናዋ 111 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ጠቁመው፤ ለ148 ሺህ 908 ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩንም ተናግረዋል።
የከተማዋን ገጽታ የቀየሩ የህዝቡን ልማት ፍላጎት የመለሱ ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸውን በዚህም ከተማዋ የተሞክሮ ተምሳሌት መሆን መጀመሯንም ጠቁመዋል፡፡
የአስተዳደሩ የ2017 በጀት ዓመት የመንግስት እና የፓርቲ የስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በከተማዋ በተለያየ እርከን የሚገኙ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026