የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

<p>የሰለጠነና ቀልጣፋ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት ለማቅረብ የማስፈፀም አቅም ማጎልበት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው - መኩሪያ ሀይሌ(ዶ/ር)</p>

Feb 10, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የሰለጠነና ቀልጣፋ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት ለማቅረብ የማስፈፀም አቅም ማጎልበት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው ሲሉ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ(ዶ/ር) ገለጹ።

ኮሚሽነሩ ፓርቲው ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በሲቪል ሰርቪስ ዙሪያ እየተደረገ ስለሚገኘው ገቢር ነበብ የፐብሊክ ሰርቪስ ሪፎርም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም ብልፅግና ፓርቲ በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው ካስቀመጣቸው ስምንት የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል አንዱ ገቢር ነበብ ፐብሊክ ሰርቪስ ሪፎርም የአገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በማድረግ በዘርፉ የነበሩ ችግሮችን መፍታት መሆኑን ተናግረዋል።


በዚህም የሰለጠነና ቀልጣፋ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት ለማቅረብ የማስፈፀም አቅም ማጎልበት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በፌደራል እና በክልል መንግሥታት የሚሰሩ ስራዎች የአደረጃጀት እና የአገልግሎት አቅርቦት የተሳለጠ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

መኩሪያ ኃይሌ(ዶ/ር) የስራ ሂደቱን የተቀላጠፈ ለማድረግ፣ ብቃት ያለውን የሰው ኃይል በማፍራት በሀገር ደረጃ የመንግስት ሰራተኛው አስተማማኝ አቅም እንዲኖረው የሚመዘንበት ስርአት እየተዘረጋ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የመንግስት ሰራተኛው በፌደራል ተቋማት ያለው ብዝሃነትንና አካታችነትን የጠበቀ የሚሆንበት ዘመናዊ የሆነ የሰው ኃይል ስምሪት በቴክኖሎጅ የታገዘ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

አክለውም እነዚህ ሰዎች ሲሰሩ በፅንሰ ሀሳብ፣ በፖሊሲ፣ በስትራቴጂ ብቻ ሳይሆን በተግባር ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።


ሪፎርሙ ገቢር ነበብ አካሄድን በመከተል ተግባርን መሰረት በማድረግ ችግሮችን የሚፈታ እና ተጨባጭ ሁኔታዎችን አገናዝቦ አመራር የሚሰጥበት ስርዓት የሚፈጥር ነው ሲሉም መኩሪያ ኃይሌ(ዶ/ር) ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ዘመናዊ አሰራር በመዘርጋት አገልግሎት በማሻሻል ህዝብ በቋንቋው የሚገለገልበት፣ በተለያየ አማራጭ አገልግሎት የሚያገኝበት ሁኔታ ለመፍጠር ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

የመንግስት ሰራተኛው በአገልግሎት አቅርቦትና ምርታማነት ላይ ያለውን ችግር ለመፍታት ትልቅ አቅም እንዳለው መረዳት መቻል እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በኢትዮጵያ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በሲቪል ሰርቪስ የተመዘገበ የመንግስት ሰራተኛ መኖሩን ያወሱት ኮሚሽነሩ በሪፎርም መንግስት ሰራተኛው በሰራው ልክ የሚጠቀም መሆኑን ተረድቶ ራሱን ማዘጋጀት አለበትም ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.