
አዲስ አበባ፤ የካቲት 02/2017(ኢዜአ)፦ የአማራ ክልል ምክር ቤት አባላት የባሕር ዳር ከተማን የኮሪደር ልማት እየጎበኙ ነው።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው የኮሪደር ልማቱን እስከ ሌሊት በመሥራት ከተማዋ ለነዋሪዎች የተመቼች፣ ጽዱ፣ ውብ እና ማራኪ እየኾነች መኾኗን ለጎብኝዎቹ አስረድተዋል።
የወጣቱን ስብዕና መገንቢያ የሚኾኑ የመዝናኛና የቤተ መጻሕፍት ሥፍራዎች መገንባታቸውንም አንስተዋል።
የምክር ቤት አባላቱ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታም እየቀየረ መሆኑን ገልጸው፤ በተለይ ጣና ሐይቅና ከተማዋን ያስተሳሰረ ሥራ መሠራቱ ለቱሪዝም ልማቱ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮሪደር ልማቱ የሥራ ባሕልን መቀየሩን የክልሉ ኮሙኒኬሸን መረጃ ያመለክታል።
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026