የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

<p>በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በየዘርፉ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስቀጠል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ይሰራል - የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ</p>

Feb 11, 2025

IDOPRESS

ቦንጋ፤ የካቲት 3/2017(ኢዜአ)፡- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በግማሽ በጀት ዓመት በየዘርፉ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስቀጠል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሰራ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ሀላፊ መስፍን ወዳጆ(ዶ/ር) በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት በተከናወኑ ሥራዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም መንግስት ለብዘሃ ኢኮኖሚ ትኩረት መስጠቱን አስታውሰው፤ በግብርና፣ በማዕድን፣ በቱሪዝምና በሌሎች የልማት ዘርፎች ህብረተሰቡን በማስተባበር በተሰሩ ሥራዎች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

መሰረተ ልማትን ከማጠናከር አንጻር በህዝብ ተሳትፎ በ116 ሚሊዮን ብር መንገድና ድልድዮችን በአዲስ የመገንባትና የመጠገን ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል።

ግንባታቸው የተጀመሩ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በማጠናቅቅ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ መሰራቱንም ተናግረዋል።

በግብርና ዘርፍ በመኸር እርሻ ከ384 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች በማልማት 17 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መቻሉንም ተናግረዋል።

የሌማት ትሩፋትን ጨምሮ በአዳዲስ የልማት ኢኒሼቲቮች ውጤቶች እየተመዘገቡ መጥተዋል ነው ያሉት።

በበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት ከ6 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን፣ ምርታማነትን ለማሳደግም የምርጥ ዘርና የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ሥራ በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።

በግማሽ በጀት ዓመት ከ25 ሺህ 247 ቶን በላይ ቡና እንዲሁም 21 ሺህ 877 ቶን የቅመማቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡንም ጠቁመዋል።

በቀጣይም በክልሉ በቡናና ቅመማቅመም የሚለማ ማሳና ምርታማነት በማሳዳግ ህብረተሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሰራ አቅጣጫ መቀመጡንም ነው የተናገሩት።

ባለፉት ስድስት ወራት ከ4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የክልሉን የልማት ግቦች ለማሳካት ሲሰራ መቆየቱን ያስታወሱት ምክትል ሃላፊው፣ ካለው የገቢ አቅም አንጻር ስራው ይጠናከራል ብለዋል።

በማህበራዊ ዘርፍ በትምህርት፣ በጤናና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተከናወኑ ሰው ተኮር የልማት ተግባራት የታየው የህዝብ ተሳትፎና የተገኙ ውጤቶች እንደሚጠናከሩም ገልጸዋል።

በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት በየዘርፉ የተገኙ ውጤቶችን በማስቀጠልና ጉድለቶችን በማረም የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የፍትህ ተደራሽነትን ማሳደግ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን መከላከል እንዲሁም የፐብሊክ ሰርቪስ ሪፎርምን ውጤታማነት ማረጋገጥ ለቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን የቢሮው ምክትል ሀላፊ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.