የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

<p>ወጣቱ  በአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን ለይቶ መስራት ላይ ማተኮር  አለበት</p>

Feb 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2017(ኢዜአ)፦ወጣቱ በመንግስት የተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎችን በመጠቀም በአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን ለይቶ መስራት ላይ ማተኮር እንዳለበት የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት አባላት ገለጹ።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት አባላት የወጣቶች ማህበር አባላት ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው ውጤታማ እንዲሆኑ መንግስት የብድር አገልግሎትና የመስሪያ ቦታ ከማመቻቸት ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል።

መንግስት የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ፖሊሲ ገቢራዊ ከማድረግ ጀምሮ የተለያዩ አስቻይ ሁኔታዎችን እየዘረጋ ይገኛል ብለዋል፡፡

በዚህም ወጣቶች በፈጠረላቸው ምቹ አጋጣሚ በመታገዝ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ አቅማቸውንና ዕውቀታቸውን በተገቢው ሁኔታ ለይተው ሊጠቀሙ ይገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ዋና ፀሐፊና የኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር አደረጃጃት ዘርፍ ኃላፊ ወጣት ይሁነኝ ማህመድ ወጣቶች የበለፀገች ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የወጣቶች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ቀዳሚ ነው ብለዋል፡፡

መንግስት የወጣቶችን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎችን በየደረጃው እያከናወነ መሆኑን ጠቅሶ፤ ወጣቱ የራሱን አቅምና ዕውቀት በመጠቀም በአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን ለይቶ መስራት እንደሚገባ ተናግሯል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወጣቶች ምክር ቤት ሰብሳቢና በኢትዮጵያ የወጣቶች ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ አባል ወጣት መሀመድ ማሀሙድ በበኩሉ፤ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ የተበታተኑ የወጣቶች አደረጃጀቶችን ወደ አንድ ማዕከል የመጡበትና የወጣቶች የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶችን በተደራጀ መልኩ ለማቅረብና መፍትሔ ለማመቻቸት ያግዛል ብሏል፡፡


የአማራ ክልል ወጣቶች ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚና የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ወጣት ዘላለም አለምባየህ በበኩሉ፤ ወጣቱ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገትና ልማት መሰረት መሆኑን አንስቷል፡፡

ሀገሪቱ የጀመረችው የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ የወጣቱ ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው፤ ወጣቱ በሰለጠነበት የሙያ መስክና ባካበተው ልምድ ጠንክሮ በመስራት ውጤታማ ለመሆን መትጋት እንዳለበት ተናግሯል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አህመድ በበኩላቸው፤ መንግስት የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸው፤ ባለፉት ሶስት ዓመታት ሰባት ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን አብራርተዋል፡፡


ወጣቶች በአካባቢያቸው ያለውን መልካም ዕድሎች በመለየትና ባሉ ምቹ አጋጣሚዎች በመጠቀም ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ጠንክረው እንዲሰሩም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.