መቱ፤ የካቲት 6/2017(ኢዜአ)፦ የቡና ምርት መጠንና ጥራት በመጨመር ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እየሰሩ መሆናቸውን በኢሉባቦር ዞን ሁሩሙ ወረዳ በቡና እድሳት ስራ ላይ የሚገኙ አርሶ አደሮች ተናገሩ።
በኢሉ ባቦር ዞን የሁሩሙ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ታምሩ ፍሪሳ ያረጁ እና ምርታማነታቸው የቀነሱ የቡና ተክሎችን እያደሱ መሆኑን ተናግረዋል።
ካላቸው የቡና ማሳ በዚህ ዓመት አንድ ሔክታር ያህሉን በጉንደላ እያደሱ እንደሆነ የገለጹት አቶ ታምሩ፤ የቡና ተክሎቹ ለረዥም ጊዜ በመቆየት ምርታማነታቸው የቀነሱ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ዮሴፍ ስለሺ በበኩላቸው ያረጁ የቡና ተክሎችን በአዲስ መተካት ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ጉልህ ድርሻ እንዳለው አንስተው፤ ይህንኑ በባለሙያዎች ታግዘው በመሥራት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሌላኛው የዚሁ ወረዳ ነዋሪ አቶ ታረቀኝ ገለታ እንዳሉት ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር የቡና እድሳት ስራውን በኩታ ገጠም እያከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።
ያረጀ ቡና ምርታማነቱ የሚቀንስ በመሆኑ ተጠቃሚ እንደማይሆኑ አክለዋል።
በዞኑ የሁሩሙ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱቃሃር ሺፋ በወረዳው በ1ሺህ 630 ሔክታር መሬት ላይ የቡና እድሳት ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።
ያረጀ የቡና ተክል ምርቱ ከመቀነስም በላይ የቡናው ፍሬ መጠንም ትናንሽ እየሆነ ስለሚሄድ ጥራት ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ገልጸዋል።
በመሆኑም የቡና እድሳት ስራ ወሳኝ ስለሆነ በአርሶ አደሮች በንቃት እየተከናወነ ነው ብለዋል።
በኢሉባቦር ዞን በተያዘው ዓመት ከ22ሺህ ሔክታር መሬት ላይ የሚገኝ ቡናን የማደስ ስራ በመደበኛ ፕሮግራም እና በኩታ ገጠም እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መልካሙ ጫሊ ናቸው።
የቡና ዕድሳት ስራው በጉንደላና በመንቀል የሚከናወን መሆኑን ጠቁመው፤ ከአጠቃላይ እቅዱ 7ሺህ 918 ሔክታር መሬት ላይ ያረጀ ቡና ተነቅሎ በአዲስ የቡና ችግኝ የሚተካ መሆኑን ተናግረዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025