አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2017(ኢዜአ)፦ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና አህጉራዊ የእሴት ሰንሰለቶችን በማዋሃድ ውጤታማ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ አቅም እንዳለው በአፍሪካ ኅብረት የኢኮኖሚ ልማት፣ የንግድ ኢንዱስትሪና ማዕድን ኮሚሽነር አምባሳደር አልበርት ሙቻንጋ ገለጹ።
ኮሚሽነሩ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በኢንዱስትሪ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም አጀንዳ 2063ትን ማሳካት የሚያስችሉ አበረታች ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።
በመረጃ ላይ የተመሰረተ ሪፖርቶችን በማውጣት ተስማሚ ፖሊሲዎች እንዲወጡ ጠንካራ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።
እንዲሁም የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናን ለመመስረት የድርድር ፊርማ ማፅድቅ እና ወደ ስራ እንዲገባ የማመቻቸት ስራ መሰራቱንም ጠቁመዋል።
አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና አህጉራዊ የእሴት ሰንሰለቶችን በማዋሃድ ውጤታማ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ አቅም እንዳለው ተናግረዋል።
ይህም በአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማትን ለማፋጠን የድርጊት መርሃ ግብሩን መተግበር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ጠቅሰው፤ ለስኬታማነቱ የሚያገለግሉ ተግባራትን ሀገራት ማከናወን እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
በአፍሪካ አህጉራዊ የእሴት ሰንሰለቶች ላይ የካርታ ስራ መሰራቱንና ከፍተኛ አቅም ያላቸው 94 የእሴት ሰንሰለቶች መለየታቸውን ተናግረዋል።
ፋርማሲዩቲካል፣ የምግብ፣ የአልባሳት እና አውቶሞቲቭ ዘርፎች ቢያንስ አምስት የአፍሪካ ሀገራትን የሚያገናኝ የእሴት ሰንስለት መኖሩን ጠቁመዋል።
እያንዳንዱ የእሴት ሰንሰለት ለሴቶች እና ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር እና ዘላቂ ልማትን በማስተዋወቅ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑንም አመላክተዋል።
ከአፍሪካ ግቦች ጋር በማጣጣም የጤና፣ የምግብ ዋስትናን ለማሻሻል እና የአፍሪካ አህጉራዊ የነጻ ንግድ ቀጣና ውድድርን በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ተስፋ ሰጪ መሆናቸው መለየቱን ገልጸዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025