የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

<p>የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ ያጠናክራል</p>

Feb 19, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የባንኩ ፕሬዚዳንት አኪንዉሚ አዴሲና(ዶ/ር) ገለጹ።

ፕሬዚዳንቱ ማህበራዊ ትስስር ባስተላለፉት መልዕክት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር ጥሩ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ባንኩ ለኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

በተለይ ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ላይ ያስመዘገበችውን ውጤት ለማጠናከር የባንኩ ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ በመልክታቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.