
አዲስ አበባ ፤የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የልማት ኢኒሼቲቭ ከ20 በላይ ፕሮጀክቶችን እያከናወነች መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ገለጹ፡፡
የአፍሪካ ቀንድ የልማት ኢኒሼቲቭ ጉባዔ የአባል አገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች እና የልማት አጋሮች በተገኙበት ተካሒዷል፡፡
ጉባዔውን በተመለከተ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
አቶ አሕመድ ሽዴ በመግለጫቸው፥ የአፍሪካ ቀንድ የልማት ኢንሼቲቭ በመሰረተ ልማት፣ በጤና፣ በድርቅ ቅነሳና በሌሎች ዘርፎች ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
ኢኒሼቲቩ ኢትዮጵያን፣ ኬንያን፣ ሶማሊያን፣ ጅቡቲን፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳንን እንደሚይዝ አመላክተዋል፡፡
በጉባዔው ባለፉት አመታት ከአጋር አካላት የተሰበሰበው የሐብት መጠንና የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ተገምግሟል ብለዋል።
እስካሁን ድረስ 9 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር መሰብሰቡንና በአፈጻጸም ደረጃም ኢትዮጵያ በተሻለ ሁኔታ እንደምትገኝ በጉባዔው መገምገሙን አመላክተዋል፡፡
በዚህም ከተሰበሰበው ሀብት ኢትዮጵያ 3 ቢሊዮን ዶላር እንድታገኝ አስችሏታል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የልማት ኢኒሼቲቭ ከ20 በላይ ፕሮጀክቶችን እያከናወነች መሆኑን ተናግረዋል።
እየተከናወኑ ካሉ ፕሮጀክቶች መካከል የአዲስ አበባ- ጅቡቲ፣ የአዲስ አበባ -በርበራ፣ የመኢሶን -ድሬዳዋ ያሉ የመንገድ፣ የመብራትና የሪጅናል ዲጅታል መሰረተ ልማቶችን ለአብነት አንስተዋል፡፡
በኢኒሼቲቩ የሚገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ከአንድ ሀገር በላይ ጠቀሜታ ያላቸው መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡
ጉባዔው በቀጣይ የልማት ትስስሩን በማጠናከር በትምህርትና በሉሎች ዘርፎች ያለውን የአባል ሀገራት ትብብር ለማጠናከር አቅጣጫ ማስቀመጡን ገልጸዋል፡፡
ለዚህም ተጨማሪ ሐብት የማሰባሰብ ስራ ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ነው የተናገሩት፡፡
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026