መቀሌ፤ የካቲት 12/2017(ኢዜአ)፡- በትግራይ ክልል በ2017/18 የምርት ዘመን የተሻለ ምርት ማግኘት የሚያስችሉ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮ ኃላፊው እያሱ አብርሃ(ዶ/ር) እንደገለፁት፤ እየተካሄዱ ካሉ የዝግጅት ስራዎች መካከል እርጥበትን ማከማቸት የሚያስችለው የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ አንዱ ነው።
የዝናብ ውሃን ወደ ከርሰ ምድር በማስረግ የእርሻ መሬት እርጥበትን የማጎልበት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀው በተለይም ከሚቀጥለው መጋቢት ወር ጀምሮ በማሳ ላይ ትኩረት በማድረግ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራው በስፋት ይከናወናል ብለዋል።
እንዲሁም ለመጪው ክረምት የሚያስፈልግ አንድ ሚሊዮን ኩንታል ዘመናዊ የአፈር ማዳበሪያ ከወዲሁ እየተጓጓዘ መሆኑን አመልክተዋል።
በክልሉ ለምርት ዘመኑ 150 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር እንደሚያስፈልግ የገለጹት የቢሮ ኃላፊው ባለፈው ዓመት የክልሉ አርሶ አደር በራሱ አቅም 55 ሺህ ኩንታል እንዲያባዛ በመደረጉ እጥረቱን እንደሚያቃልለው አብራርተዋል።
በልግ አብቃይ ከሆኑ ወረዳዎች በተጨማሪ አርሶ አደሮች ማሳቸውን በአዝመራ ለመሸፈን እያከናወኑ መሆኑን በመግለፅ እየዘነበ ያለውን ዝናብ ወደ ማሳ የማስገባት ስራ በስፋት እየተካሄደ ነው ብለዋል።
በመጪው ክረምት ከ800 ሺህ በላይ ሄክታር መሬትን በተለያዩ አዝርእቶች በመሸፈን 24 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም ቢሮ ኃላፊው አብራርተዋል።
በ2016/17 የምርት ዘመን ከክልሉ 13 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን ቢሮው መግለፁ ይታወሳል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025