ወልዲያ፤ የካቲት 12/2017(ኢዜአ)፡- በሰሜን ወሎ ዞን 19 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የምግብ ሰብል በመስኖ የማልማት ስራ እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
ከሚለማው መሬት 432 ሺህ 203 ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅም መምሪያው ገልጿል።
በሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የመስኖ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ቡድን መሪ አቶ አለባቸው መራዊ፤ አርሶ አደሩን በመስኖ ልማት በማሰማራት የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል።
በዚህም ዘንድሮ ከ20 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት ታቅዶ በተደረገ ጥረት እስካሁን 19 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር የመሸፈን ስራ መከናወኑን አስታውቀዋል።
ከ100 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን በማሳተፍ በሚካሄደው የመስኖ ልማት 12ሺህ ሄክታሩ በበጋ ስንዴ የለማ ሲሆን፤ ቀሪው በሽንብራ እና በአትክልትና ሌሎች ሰብሎች የተሸፈነ መሆኑን ተናግረዋል።
በመስኖ ከሚለማው አጠቃላይ መሬትም 432 ሺህ 203 ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ጠቁመው፤ ምርታማነቱን ለማሳደግ 8ሺህ 169 ኩንታል ምርጥ ዘርና 28ሺህ 946 ኩንታል ማዳበሪያ ጥቅም ላይ ውሏል ብለዋል።
በስንዴ ከለማው መሬት ውስጥ ሰባት ሺህ ሄክታሩ በኩታ ገጠም የተሸፈነ፣ አዳዲስ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎች የተተገበሩበት መሆኑንም አስረድተዋል።
በዞኑ የጉባላፍቶ ወረዳ አርሶ አደር ዘውዱ ስጦቴ በሰጡት አስተያየት፤ በግማሽ ሄክታር መሬታቸውን በስንዴ ሰብል በመሸፈን በማልማት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ለመስኖ ልማትግብዓት ዘንድሮ ቀድሞ መድረሱን ጠቁመው፤ አሁን ላይ ቡቃያውን በማረምና ተባይ በመከላከል እንክብካቤ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
በመስኖ ካለሙት ግማሽ ሄክታር መሬት እስከ 21 ኩንታል ስንዴ ለማምረት አቅጄ እየሰራሁ ነው ያሉት ደግሞ አርሶ አደር ተሾመ አስራዴ ናቸው።
የስንዴ ምርት ባልተለመደበት አካባቢያቸው ባለፈው ዓመት ጀምረው ባገኙት ተሞክሮ ዘንድሮ በቂ ምርት በማምረት ከራሳቸው ፍጆታ የተረፈውን ለገበያ ለማቅረብ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
በሰሜን ወሎ ዞን ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ከለማው 19ሺህ ሄክታር መሬት ላይ 356 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን በወቅቱ ተገልጿል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025