አዲስ አበባ፤ የካቲት 12/2017(ኢዜአ)፦ለማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ መሳካት እና የሀገሪቱን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የንግድ ከባቢ ሁኔታ መሻሻል ወሳኝነት እንዳለው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለፀ።
ሁለተኛው የንግድ ከባቢ ሁኔታ ምቹነት የሪፎርም ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ዛሬ ተካሄዷል።
በዚሁ ወቅት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብታዊ እድገት ለማፋጠንና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ መንግስት ከምንጊዜውም በላይ የግሉን ዘርፍ ያሳተፉ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።
መንግስት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም ስራ ፈጣሪዎች በኢኮኖሚው ዘርፍ የላቀ ተሳትፎ የሚያደርጉበትን ምቹ መደላድል ለመፍጠር የሚያስችል ተግባር እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ለግሉ ዘርፍ ተዋናዮች ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ በመፍጠር ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ ማገዝ አለብን ብለዋል።
ሚኒስቴሩ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚሰማሩ ባለሀብቶችን ውጤታማነት ለማሳደግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
በዚህም በዛሬው እለት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለግሉ ዘርፍ ምቹ የስራ ከባቢን ለመፍጠር ሁለተኛው የንግድ ከባቢ ሁኔታ ምቹነት ሪፎርም መርኃ ግብር በይፋ መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡
በመርኃ ግብሩ ውጤታማነቱን ለማሳለጥ የሚያስችል ምክክር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መደረጉን ተናግረዋል።
ሁለተኛው ሪፎርም የግሉ ዘርፍ አንቀሳቃሾች ከፖሊሲ አኳያና ከመሰረተ ልማት ጋር በተያያዘ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠትና ኢንቨትመንትን ለማሳደግ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰዋል።
ለግሉ ዘርፍ ምቹ ከባቢን ለመፍጠር የሚደረጉ ማሻሻያዎች በዋናነት እንደ ሀገር የጀመርናቸውን ሪፎርሞች ለማሳለጥ ያስችላሉ ብለዋል፡፡
በአጠቃላይ ማሻሻያዎቹ የሀገሪቱን የንግድ ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉ 62 ኢኒሼቲቮች የተለዩበት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ኢንሼቲቮች ተጨማሪ የስራ እድል ለመፍጠር፣ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብና የኢንተርፕራይዞችን ቁጥር ለመጨመር ያስችላሉ ሲሉ አስታውቀዋል፡፡
ኢንሼቲቮቹ ባለሃብቶች በስራቸው የሚያስፈልጓቸውን ጉዳዮች በተቀላጠፈ መንገድ ለመጨረስ አቅም ይፈጥራሉ ሲሉም አክለዋል።
ኢንሼቲቮቹ ከንግድ ፣ከግብር ፣ከገቢዎች ፣ ከመሰረተ ልማት ፣ከአገልግሎት አሰጣጥ ፣ከዋስትና ፣ከስራ ደህንነት ፣ ከፋይናንስ አቅርቦት ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
የምክክሩ ተሳታፊዎች የግሉን ዘርፍ ምርትና ምርታማነት ለማጎልበት የሚያግዙ ተግባራትን በተናበበና በተቀናጀ መልኩ መስራት አለብን ብለዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025