ባሕር ዳር፤ የካቲት 13/2017 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የግብርና ምርት አምራችና አስመራች ግንኙነት አዋጅ የግብርና ምርታማነትን የሚጨመርና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል እንደሆነ ተገለፀ።
የግብርና ምርት አምራችና አስመራች ግንኙነትን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት ስልጠና በባህር ዳር ከተማ እየተሰጠ ነው።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አጀበ ስንሻው እንዳሉት የአምራቶችና አስመራቾች መስተጋብር ለግብርና ምርታማነት ዕድገት ይበጃል።
አዋጁ አምራቹ የሰብል ግብዓት፣ ቴክኖሎጂና ስልጠና ከአስመራች እንዲያገኝ ብሎም ምርቱን በቀጥታ ለአስመራች እንዲያስረክብ ያግዘዋል ብለዋል።
አስመራች ደግሞ ያስመረተውን ምርት በቀጥታ ተቀብሎ ለኢንዱስትሪም ሆነ ለውጭ ገበያ እንዲያቀርብ ዕድል ይሰጠዋል ነው ያሉት።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር አስተዋጽዖ ያላቸው ሁለት ረቂቅ አዋጆችን አጸደቀ
በዚህም አዋጁ የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ ሁለቱን ወገን ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ ለትግበራው በጋራ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም፤ አዋጁ አምራቾችና አስመራቾች ውል ገብተው ለጋራ ተጠቃሚነትን የሚሰሩበትና ለሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አሻራቸውን እንዲያሳርፉ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።
የክልሉ ህብረት ሥራ ማህበራት ማስፋፊያ ባለስልጣን የግብዓትና ግብይት ዳይሬክተር አቶ አለምዘውድ ስሜነህ በበኩላቸው አዋጁ ጥራትና ብዛት ያለው ምርት ለማምረት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
በግብርናው ዘርፍ አምራችና አስመራች ከዘርፉ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኙ የሚያስችል አዋጅ ተግባራዊ ሊደረግ ነው
ለሁለት ቀናት በሚቆየው ስልጠና ከክልል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር የባለድርሻ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025