ባህርዳር፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በግንባታ ኢንዱስትሪው ዘርፍ ዘመን ተሻጋሪ አሻራዎቹን ለማሳረፍ ይበልጥ መዘጋጀት እንዳለበት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ከተሞች ዘርፍ አስተባባሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ አሕመዲን መሀመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
የአማራ ሕንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ስያሜውን ወደ "ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን" በመቀየር የአደረጃጀትና የንግድ ትውውቅ መድረክ በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል።
በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ከተሞች ዘርፍ አስተባባሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሃላፊና የኮርፖሬሽኑ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አሕመዲን መሀመድ(ዶ/ር)፤ ኮርፖሬሽኑ በግንባታ ኢንዱስትሪው ዘመን ተሻጋሪ አሻራዎቹን ለማሳረፍ የላቀ ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
የመፈጸምና የተወዳዳሪነት አቅሙን በማሳደግም ትልቅ ራዕይ አንግቦ መነሳቱን ጠቁመው፤ ለተግባራዊነቱ የስራ አመራር ቦርዱ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
በመሆኑም ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በግንባታ ኢንዱስትሪው ዘርፍ ዘመን ተሻጋሪ አሻራዎቹን ለማሳረፍ ይበልጥ መዘጋጀት ይኖርበታል ነው ያሉት።
የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ በበኩላቸው፤ ኮርፖሬሽኑ የገበያ ክፍተትን በመሙላት ከክልሉ አልፎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተልዕኮውን በአግባቡ እየፈፀመ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም ከፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ተነስቶ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ አመስግነው፤ በቀጣይም ለተሻለ እድገትና ስኬት እንዲበቃ እገዛ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
የአደረጃጀትና የስም እንዲሁም የምልክት(ሎጎ) ለውጥ ማድረጉም ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት መፈፀም የሚያስችለው መሆኑን አንስተዋል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ግርማ፤ ኮርፖሬሽኑ በተለይም በህንጻ፣ በአስፋልትና በጠጠር መንገዶች ግንባታ በብቃት በማከናወን የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።
የአደረጃጀት፣ የስያሜና የምልክት ለውጥ ማድረጉም እሴቶችን በማጠናከር ተወዳዳሪነትና የገበያ አድማሱን ለማስፋት የሚያግዘው ይሆናል ብለዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025