አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2017(ኢዜአ)፡- በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ በጋራ የመስራት ፍላጎት እያሳዩ መሆኑን የኢትዮያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ገለጹ።
አየር መንገዱ በየጊዜው ዓለም አቀፍ አድማሱን በማስፋት ላይ መሆኑንም ተናግረዋል።
የአፍሪካ አህጉርን ደግሞ በአየር ትራንስፖርት የማስተሳሰር ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል ነው ያሉት፡፡
በአሁኑ ወቅትም በርካታ የአፍሪካ ሀገራት በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ከአየር መንገዱ ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎቶች እያሳዩ መሆኑን ገልጸዋል።
በቅርቡ የናይጄሪያ የአቪዬሽንና የኤሮስፔስ ልማት ሚኒስትር አየር መንገዱን መጎብኘታቸውንና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ናይጄሪያ የሚያደርጋቸውን በረራዎች ማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ተናግረዋል።
ይህም ለአየር መንገዱም ሆነ ለናይጄሪያውያን መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር መሆኑ ነው ዋና ስራ አስፈጻሚው የገለጹት።
በቀጣይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ አህጉርን በአየር ትራንስፖርት ለማስተሳሰር የጀመረውን ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመታደም አዲስ አበባ የመጡ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና ከፍተኛ ኃላፊዎች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችሉ ፍሬያማ ውይይቶች መድረጋቸውንም አውስተዋል።
በዚህም ሀገራቱ አየር መንገዶቻቸውን ለማሳደግና አየር መንገድ የሌላቸው ሀገራት ደግሞ ማቋቋም በሚቻልባቸው ሂደቶች ላይ ውይይቶች መደረጋቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት በአህጉሪቱ ከ66 በላይ ከተሞች ይበራል።
ይህም የቱሪዝም፣ የንግድ፣ የሰዎች እንቅስቃሴን በማሳለጥ፣ በምጣኔ ሃብት፣ በማህበራዊና በዲፕሎማሲ መስክ የሀገራቱን ትብብርና ተጠቃሚነት በማሳደግ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025