አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2017(ኢዜአ)፡- የኮሪያ ሪፐብሊክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት እድል በመጠቀም መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በኮሪያ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሴ ዳልኬ ጥሪ አቀረቡ።
የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድል የሚያስተዋውቅ የኢንቨስትመንት ፎረም በኮሪያ ሪፐብሊክ ሴዑል ተካሄዷል።
በፎረሙ ላይ ከ200 በላይ የሚሆኑ የካምፓኒ ባለቤቶች እና ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በኮሪያ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሴ ዳልኬ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አማራጮች አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የተሻለ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ማበረታቻዎች ያላት ሀገር ናት ያሉት አምባሳደሩ ባለሃብቶቹ ይህን እድል በመጠቀም በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።
ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታን ለመፍጠር በኢትዮጵያ መንግስት የተደረጉ የቢዝነስ ፖሊሲ ማሻሻያች፣ ዋና ዋና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች እና ምቹ የንግድ ከባቢያዊ ሁኔታዎች የተመለከቱ ጉዳዮች በፎረሙ ላይ ቀርበዋል።
በጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የተሰማራው የሺንቴስ ኩባንያ ተሞክሮውን ለባለሃብቶቹ አቅርቧል።
ባለሀብቶቹ ከተደረገው ገለጻ ኢትዮጵያ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ያላት አገር እንደሆነች ለመገንዘብ መቻላቸውን ተናግረዋል።
በቀጣይ በኢትዮጵያ የቅድመ-ኢንቨስትመንት ጉብኝት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን በሴዑል የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025