የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

<p>በክልሉ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የማሳ ላይ እንክብካቤ ስራዎችንና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ባህል ማድረግ ይገባል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)</p>

Feb 28, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ በክልሉ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የማሳ ላይ እንክብካቤ ስራዎችንና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ባህል ማድረግ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገልጸዋል።

ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር ሊታረስ የሚችሉ ሰፊ መሬቶችን በመለየት የማሳ ሽፋንን ማሳደግ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ የ6 ወራት የግብርና ልማት ስራዎች አፈጻጸምና የቀጣይ በልግ እርሻ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በመድረኩም በእርሻ ዘርፍ፣ በግብርና ግብዓትና በተፈጥሮ ሀብትና መሬት አጠቃቀም ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) አመራሩና ባለሙያው አርሶ/አርብቶ አደሩ ጋር የሚሰጠውን ሙያዊ ዕገዛ የበለጠ ማጎልበት ይገባዋል ብለዋል፡፡


የግብርና ምርት ምርታማነትን ለማሳደግ የአፈር ማዳበሪያ አጠቃቀም ስርዓት ላይ ልዩ ትኩረት ሊሰጠውም እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

በክልሉ በሚለሙ ዋና ዋና ሰብሎች ላይ በሄክታር የሚገኘውን ምርታማነት ለማሳደግ የማሳ ላይ እንክብካቤ ስራዎችንና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ባህል ማድረግ ዋነኛ ተግባራችን ሊሆን ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ግብርናን ለማዘመን ሜካናይዜሽን ስራዎች ያሉባቸውን ችግሮች በመለየት ልዩ ትኩረት በመስጠት ሊሰራበት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

የአፈር ማዳበሪያ ዕዳ አመላለስን በተመለከተ ዕዳ ያለባቸው ዞኖች ፈጥነው ገንዘቦችን በመሰብሰብ ወደ ባንክ ገቢ ማድረግ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል፡፡


በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ነጋ አበራ በሰጡት አስተያየት አመራሩና ባለያው በግብርና ልማት ስራዎች ላይ አቅሙን አሟጦ በመጠቀም ለምርትና ምርታመነት የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ተሰማ በበኩላቸው በግብርና ልማት ስራዎች ላይ አደረጃጀቶችን ኃላፊነት በተሰማው መንገድ በመጠቀም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡


የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በቀሪ 6 ወራት የሚፈጸሙ የግብርና ልማት ስራዎች ብልጽግናን ለማረጋገጥ መሰረት በመሆናቸው በክልሉ መንግስት የተነደፉ የተለዩዩ ግብርና ኢኒሼቲቮችን ውጤታማ ለማድረግም ያግዛሉ ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.