
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- በ2018 ዓ.ም በትምህርት ቤቶች የፋይዳ እና የልደት ምዝገባን ቅድመ ሁኔታ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ከመስከረም 2017 ዓ.ም ጀምሮ ያለው የፋይዳ ምዝገባ አፈፃፀም ግምገማ እና የቀጣይ የተማሪዎች ምዝገባ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የዜጎችን መረጃ በማደራጀት በአንድ ቋት መያዝ ከሚያስችሉ አሰራሮች መካከል የፋይዳ እና የልደት ምዝገባዎች ተጠቃሾች ናቸው።
በአሁኑ ወቅትም የፋይዳ ምዝገባ በትምህርት ቤቶች ጭምር በንቅናቄ ለማካሔድ ስራ መጀመሩን አመላክተዋል፡፡
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ቤቶች የፋይዳ እና የልደት ምዝገባ ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ቅድመ ሁኔታ እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡
በትምህርት ቤቶች ፋይዳ መታወቂያ እንደ ስኮላርሽፕ፣ ምገባ፣ የትራንስፖርት ሰርቪስ እና የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ለማግኘት እንደሚረዳ ተናግረዋል።
ምዝገባውን እስከ ሰኔ 2017 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ለማጠናቀቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዮዳሄ አርዓያስላሴ በበኩላቸው፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የፋይዳ ምዝገባ ከተጀመረ ወዲህ በርካታ ዜጎችን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
ባለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ወደ 4 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች ለፋይዳ መታወቂያ መመዝገባቸውን አመላክተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር)፣ በመዲናዋ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ሊያስተሳር የሚችል የኢ-ስኩል ሶፍትዌር ለመጀመር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዛሬ በይፋ የተጀመረው የተማሪዎች የፋይዳ ንቅናቄ የኢ-ስኩል አሰራር በተገቢው መንገድ ለመተግበር ትልቅ ግብዓት እንደሚሆን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በበኩላቸው የትምህርት ቤቶች የፋይዳ ምዝገባ በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን ይሰራል ብለዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አለማየሁ እጅጉ፤ ንቅናቄው በውጤት እንዲጠናቀቅ የግንዛቤ ፈጠራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
በንቅናቄው ወቅት ለሚያጋጥሙ ችግሮች ፈጥኖ ምላሽ ለመስጠት በየጊዜው መረጃ መለዋወጥ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026