አርባምንጭ፤የካቲት 23/2017ኢዜአ)፦የአድዋን ድል ጀግንነት በድህነት ላይ በመድገም አገራዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ።
129ኛው የአድዋ ድል በዓል በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በፓናል ውይይት እየተከበረ ነው።
በፓናል ውይይቱ ላይም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳይ ምክትል ፕሬዚዳንትና የፕሬዚዳንቱ ተወካይ ኢንጂነር ቦጋለ ገብረማሪያም (ዶ/ር)፥ የጥንት አባቶቻችን በማበር የተቀዳጁት የአድዋ ድል ለጥቁር ህዝቦች ነፃነትን ማረጋገጡን አውስተዋል።
የአሁኑ ትውልድም የአድዋን ድል ጀግንነት በድህነት ላይ በመድገም አገራዊ ብልጽግናን ሊያረጋግጥ ይገባል ብለዋል።
በአባይ ወንዝ ጉዳይ ሀጋራዊ የጋራ ትርክት መገንባቱን ጠቅሰው፥ አንድነታችንን ይበልጥ በማጠናከር ድህነት ላይ ድል መቀዳጀት ይጠበቅብናል ሲሉ አመልክተዋል።
ከተባበርን የሀገር ሉዐላዊነትን ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ሉዐላዊነትን ማረጋገጥ እንደምንችል አድዋ ማሳያችን ነው ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ታሪክ እየዘከርን ታሪክ በመፃፍ ለመጪው ትውልድ የተሻለች ሀገር የማውረስ ታሪካዊ ኃላፊነት አለብን ብለዋል።
ከአድዋ ድል አንድነት፣ቆራጥነትና ሀገር ወዳድነትን ልንማር ይገባል ያሉት ደግሞ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተክሉ ወጋየሁ ናቸው።
ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን በመተው ችግሮቻችንን በውይይትና በምክክር መፍታት አለብን ሲሉም አክለዋል።
የጋሞ እና ጎፋ ዞኖች ጥንታዊ ኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር ሊቀመንበር አቶ ተስፋዬ ገመዳ በበኩላቸው፥ የአድዋ ድል የህብርና የአንድነት ውጤት ነው ብለዋል።
ቀደምት አባቶቻችን ዘር፣ብሔር ፥የሃይማኖት ልዩነት ሳያግዳቸው ደማቸውን አፍሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው ኢትዮጵያን አኑረዋል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያን ከነ ሙሉ ክብሯ ለመጪው ትውልድ የማስተላለፍ አደራ አለብን ሲሉም አመልክተዋል።
በፓናል ውይይቱም "በኢትዮጵያ ሴቶች የጀግንነት ውሎ እና በዝክረ አድዋ አላማ" ላይ ያተኮሩ ሁለት ሰነዶች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።
በበዓሉ ላይም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ፣ ጥንታዊት አርበኞች፣የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025