የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

<p>የአዲስ አበባ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አመራሮች እና አባላት የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎበኙ</p>

Mar 3, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 23/2017(ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አመራሮች እና አባላት የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን መጎብኘታቸውን ከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።


ጽህፈት ቤቱ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አባላቶቹ ማዕከሉ የንግዱን ማህበረሰብ በንግድ ስርዓት ውስጥ በማስተሳሰር ከተቀረው ዓለም ጋር ተወዳዳሪነታቸው እንዲጨምር የሚያስችል መሆኑን በጉብኝቱ ወቅት መናገራቸውንም ገልጿል።

ማዕከሉ ከሀገር አልፎ በዓለም ደረጃ ሀገር በቀል ምርቶችን ለማስተዋወቅ እና ከተማችንን የቱሪዝም፣ የኮንፈረንስ እና የኤግዚቢሽን ማዕከል ለማድረግ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸው በተሰራው ስራ መደሰታቸውን መናገራቸውንም ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.