መቱ ፤የካቲት 25/2017 (ኢዜአ)፡-መቱ ዩኒቨርሲቲ በምርምርና እና ማኅበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ እያከናወናቸው ባሉ ተግባራት የተሻሻሉ የሰብል፣ የፍራፍሬና የእንስሳት ዝሪያዎችን ወደ አርሶ አደሩ ለማድረስ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራው በተጓዳኝ ማህበረሰብ አቀፍና የቴክኖሎጂ ሽግግር ሀገራዊ ተልዕኮዎችን ለመወጣት እንደሚሰራም ገልጿል።
የዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ፣ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት በድሉ ተካ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ከዋናው ተልዕኮዎቹ በተጓዳኝ በዘመናዊ ግብርናና የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።
በተለይም በግብርናው ዘርፍ የምርምር ውጤቶች የሆኑና ምርታማነታቸው የተሻለ የፍራፍሬ፣ የሰብልና የእንስሳት ዝሪያዎችን ወደ ማኅበረሰቡ ለማድረስ የሚያስችለውን ስራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
የተሻሻሉ የጤፍና የበቆሎ፣ የአቮካዶና የፓፓያ እንዲሁም የበግና የዶሮ ዝሪያዎችን ለማውጣት እያደረገ የሚገኘው የምርምር ስራን በማሳያነት ያነሱት በድሉ(ዶ/ር) በዚህም የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚቻል አብራርተዋል።
በሌላ በኩል በዞኑ በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የመጻህፍት እጥረት ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የዲጂታል ቤተ-መጻህፍት ድጋፍ በማድረግ የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ የበኩሉን ጥረት እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በዩኒቨርሲቲው የእንስሳት ሳይንስ መምህር ሲሳይ ለገሰ በበኩላቸው መቱ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት በአከባቢው ከሚገኙ የበግ ዝሪያዎች የተሻለ ዝሪያ በማውጣት ለሕብረተሰቡ ለማድረስ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በሌሎችም መስኮች ተመሳሳይ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን የገለጹት መምህሩ፤ ውጤታማ የሆኑ ዝሪያዎቹ በኤክሰቴንሽን ወደ ማሕበረሰቡ እንዲደርሱ የሚያደርግ መሆኑንም ተናግረዋል።
አቶ የኋላሻት ገዛኸኝ እና ወይዘሮ አልማዝ ሲሳይ ደግሞ ዩኒቨርሲቲው በመቱ ወረዳ በአከባቢው ከሚገኙ ዝሪያዎች የተሻለ ዝሪያ ለማውጣት እያከናወነ በሚገኘው ስራ ተጠቃሚ በመሆን ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች ናቸው።
ዩኒቨርሲቲው ሕብረተሰቡን በማሳተፍ የተሻለ ምርት የሚሰጡ ዝሪያዎችን ለማውጣት እያከናወነ ከሚገኘው ስራ መልካም ነገር እንደሚጠብቁም ተናግረዋል።
አቶ በዳሳ ሺንኬ በበኩላቸው መቱ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ በሚችሉ የግብርና ስራዎች ላይ ከስልጠና ጀምሮ ምርጥ የሰብል እና የፍራፍሬ እንዲሁም የእንስሳት ዝሪያዎችን ወደ ማኅበረሰቡ ለማድረስ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራት ተስፋ የሚጣልባቸው ናቸው ብለዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025