አዲስ አበባ፤ የካቲት 24/2017 (ኢዜአ)፡- 100 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ አፈጻጸም 78 ነጥብ 2 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
የፕሮጀክቱ ግንባታ በታህሳስ ወር 2013 ዓ.ም ከዴንማርክ መንግሥት በተገኘ ብድር እና ዕርዳታ ከ146 ሚሊዮን ዩሮ በላይ በጀት ተጀምሯል።
የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፈቃዱ አብርሃም ኃይል ማመንጫው እያንዳንዳቸው 3 ነጥብ 46 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም ያላቸው 29 የንፋስ ተርባይኖች አሉት።
የ22 ተርባይኖች ተከላ መጠናቀቁንና የ20ዎቹ ተርባይኖች የቅድመ ፍተሻ ሥራ መከናወኑን አመልክተዋል።
እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ የኃይል ማመንጫው የባለ 230 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያ የሲቪል ሥራ ከ95 በመቶ በላይ እንዲሁም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራ ከ60 በመቶ ደርሷል።
እያንዳንዱን ተርባይን የሚያገናኙ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በሥራ ተቋራጩ ምክንያት መዘግየት አፈጻጸሙም 54 በመቶ ላይ እንደሚገኝና አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም 78 ነጥብ 2 መድረሱን አመልክተዋል።
የግንባታው ሥራ ተቋራጭ ሲመንስ ጋሜሳ ሪኒዌብል ኢነርጂ የሳይት ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ኤድዋርዶ ጎንዛሌዝ አሁን ላይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም መልካም በሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ቀሪ ሥራዎችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025