
አዲስ አበባ፤ የካቲት 24/2017(ኢዜአ)፦ የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የኢኮኖሚ አቅም መሆን በሚያስችል መልኩ የተገነባ መሆኑን የተፎካካሪ ፓርቲ እና የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና የሲቪል ማህብረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች የአዲስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል።

የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የፋይናንስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክፍለ ማርያም ሙሉጌታ፤ ማዕከሉ መዲናዋን ውብ ገጽታ የማላበስ አካል መሆኑን ገልጸዋል።
የመዲናዋን ግዙፍ ፕሮጀክቶች አለማድነቅ ንፉግነት ነው ያሉት አቶ ክፍለ ማርያም፤ ሁለንተናዊ ሀገራዊ ለውጥ የሚረጋገጠው በብርቱ ስራና በትብብር መርህ ነው ብለዋል።
ለማዕከሉ ግንባታ ሂደት ሚና የነበራቸውን አካላትም አመስግነዋል።

የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ የአደረጃጀትና የአቅም ግንባታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙባረክ ረሽድ፤ በዲፕሎማቲክ መዲናዋ የተገነባው ማዕከሉ ዓለም አቀፍ ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን በመጥቀስ አድንቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማና የፌደራል ዕድሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ታምራት ገብረ-ማርያም፤ የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን ገልጸዋል።

ማዕከሉ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የንግድ ትርዒትና ባዛር ሁነቶችን ማስተናገድ አቅም እንዳለው በምልከታቸው እንዳረጋገጡ ተናግረዋል።
የአዲስ ትውልድ ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ቤዛ ተሰማ፤ ማዕከሉ የኢትዮጵያን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማጉላት የሚያስችል አቅም እንዳለው መታዘባቸውን ገልጸዋል።

የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች እንዳሉት ማዕከሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂና ተያያዥ መሰረታዊ ግብዓቶችን በማሟላት ምርትና አገልግሎቶችን በብቃት ማስተናገድ በሚያስችል መልኩ ተገንብቷል።
ማዕከሉ በኢትዮጵያ የነበረውን ደረጃውን የጠበቀ የንግድ ኤግዚቢሽንና ባዛር ማስተናገጃ ስፍራ ጥያቄ በመፍታት ለሀገር ኢኮኖሚ ሌላ አቅም ነው ብለዋል።
በንግድና ኢንቨስትመንት ማህብረሰብ ትስስር በመፍጠር እና ለግብይት መሳለጥ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ነው ያሉት።
የኢንዱስትሪ መስፋፋት እና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ነጻነት ለማረጋገጥ፣ የረጅም ጊዜ የኢን...
Jun 4, 2026
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 20/2018(ኢዜአ)፦ በአምስት ሚሊየን የኢትዮ-ኮደርስ መርሃ ግብር በመታገዝ በዲጂታል ክህሎት ራሳቸውን እያበቁ መሆናቸውን አስተያየታቸውን...
Jun 1, 2026
አዳማ፤ግንቦት 16/2018(ኢዜአ)፦በክልሉ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ለአሰራር ማሻሻያና ለተቋማት ግንባታ ትኩረት መሰጠቱን በብልፅግና ፓርቲ የኦ...
May 25, 2026
ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመ...
May 15, 2026